Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 21 January 2012 11:21

ለአሰፋ ጐሳዬ መታሰቢያ ቤተ - መፃህፍት የመጽሐፍ ስጦታ ተደረገ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የመጽሐፍ ስጦታ ተደረገ

በአገር ውስጥ ተማሪ እያለሁ በአሰፋ ጐሳዬ መታሰቢያ ቤተ መፃሕፍት እገለገል ነበር ያለው ወጣት ኤልያስ ወልደ አማኑኤል የአሜሪካን አገር ትምህርቱን አጠናቆ ሲመለስ በግል ይገለገልባቸው የነበሩ  የአካውንቲንግና የኮምፒዩተር ሳይንስ መፃሕፍትን ለቤተ መፃሕፍቱ አበረከተ፡፡ ሌሎች ጓደኞቹም ተመሳሳይ ልግስና የማድረግ እቅድ እንዳላቸው ወጣት ኤልያስ ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል የተለያዩ የኪነጥበብ ሥራዎችን በጋራ በመሥራት የሚታወቁት ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠና ኤሚ እንግዳ “የፈላስፎች ጉባኤ” በሚል ርዕስ የአጭር ልቦለዶች ስብስብ መጽሐፍ አሳትመው ለአንባቢያን አቅርበዋል፡፡ 244 ገፆች ያሉት መጽሐፍ ዋጋው 29 ብር ከ99 ሳንቲም ነው፡፡

 

 

Read 13937 times Last modified on Saturday, 21 January 2012 12:07