Saturday, 25 April 2015 11:02

“የምስጢር መንትዮች” መፅሀፍ ተመረቀ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(2 votes)

በተዘራ አስናቀ የተደረሰውና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው “የምስጢር መንትዮች” ታሪካዊ ልብወለድ መፅሐፍ በትላንትናው ዕለት በሩሲያ የሳይንስና የባህል ማዕከል ተመርቋል፡፡ መፅሃፉ የማህበረሰባችንን እውነተኛ ገፅታ፣ ድህነት፣ ኋላቀር አስተሳሰብና የባህል ተፅዕኖዎች እያደረሱ ያሉትን ውጣ ውረድ አጉልቶ ያሳያል ተብሏል፡፡ በምረቃ ስነስርአቱ ላይ የተለያዩ የጥበብ ባለሙያዎች ግጥም፣ ወግና መነባንብ ያቀረቡ ሲሆን ኮሜዲያኖችም ታዳሚውን አዝናንተዋል፡፡ በ242 ገፆች የተመጠነው መፅሐፉ፤ በ38 ብር እየተሸጠ ነው፡፡

Read 1610 times