Saturday, 21 January 2012 10:45

የደራሲያን ምስጢራዊ አሟሟት

Written by  ብርሃኑ ሰሙ
Rate this item
(1 Vote)

“የፈላስፎች ጉባኤ” በያዝነው ሳምንት ከማተሚያ ቤት ወጥቶ ለአንባቢያን የቀረበ መፅሐፍ ነው፡፡ በጋዜጠኝነታቸው የሚታወቁት የኤሚ እንግዳና የጥበቡ በለጠ 11 የልቦለድ ስብስቦችን የያዘው መፅሐፍ በመግቢያው “የስነ ፅሁፍን መስቀል ተሸክመው ለዚህ ያበቁን ጠቢባንን አንዴ እናስታውሳቸው” በሚል መነሻ እስከ ሞት ድረስ መስዋዕትነት የከፈሉ የኪነጥበብ ሰዎችን ያስተዋውቃል፡፡
“ሕይወቴ (ግለ ታሪክ)” በሚል ርዕስ በ2001 ዓ.ም በታተመውና የደራሲ ተመስገን ገብሬን ህይወትና ሥራ በሚያስቃኘው መፅሐፍ ውስጥም በተመሳሳይ ሁኔታ በተቀነባበረ መልኩ ስለሞቱ የኪነ ጥበብ ሰዎች ይነገራል፡፡ በሁለቱም መፃህፍት ውስጥ በአንዱ በደራሲነት በሁለተኛው በአርታኢነት የተሳተፈው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ሰፋ ያለ ጥናት ያደረገ ይመስላል፡፡ የሆነ ሆኖ አሟሟታቸው ሚስጢር ስለሆነ 10 ያህል የኪነ ጥበብ ሰዎች ሁለቱ መፃህፍት መረጃውን ለአንባቢያን ማሸጋገሪያ ድልድይ ሆነዋል፡፡
“የጉለሌው ሰካራም” የሚል አጭር ልቦለድ ፅፎ በ1941 ዓ.ም ለአንባቢያን በማቅረቡ በዘርፉ ጀማሪ በመሆን ታሪክ የመዘገበው ደራሲ ተመስገን ገብሬ፤ ለሞቱ ምክንያት የሆነው ህመም መነሻው የተመረዘ ምግብ እንዲበላ በመደረጉ እንደሆነ ብዙ ሰዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ደራሲ ተመስገን ገብሬ የተመረዘ ምግብ እንዲበላና እንዲሞት የተፈለገበት ምክንያት ምንድነው? በሚል ግለ ታሪኩን የያዘው መፅሐፍ ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል፡፡
ደራሲ ተመስገን ገብሬ በራሱ የሚተማመን ሰው ነበር፡፡ ለንጉሥ ኃይለሥላሴና ለቤተመንግሥታቸው የቅርብ ሰው ነው፡፡ የንጉሡን ልጆች ያስተምር ነበር፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት በእንግሊዝ ለነበሩት አፄ ኃይለሥላሴ ደብዳቤ እየፃፈ በአገር ውስጥ ያለውን መረጃ ያቀብላቸዋል፡፡ ጠላት ከተባረረ በኋላ ሁሉም ንጉሡ ዘንድ እየቀረበ ሹመትና ሽልማት ሲጠይቅ ደራሲ ተመስገን ገብሬ የሚያስፈልኝን በራሴ ሰርቼ ማግኘት እችላለሁ ነበር ያለው፡፡ በአንዳንድ ጉዳይ ከባለስልጣናት ጋር ተከስሶ ይረታ ነበር፡፡ እነዚህ ጠንካራና ብርቱ ጐኖቹ ጠላት እንዲያፈራ ምክንያት ሆነውት ብቻ አልቀሩም፡፡ የተመረዘ ምግብ እንዲመገብ በስውር ተቀነባብሮ ሞቱ እንዲፋጠን ተደረገ፡፡
የደራሲ ተመስገን ገብሬን አሟሟት በሚተርከው ምዕራፍ ውስጥ ምክንያቱ በግልፅ በሚታወቅና በማይታወቅ አፈፃፀም በተቀነባበረ ዘዴ ለሞት የተዳረጉ ናቸው በሚል የሚከተለው መረጃ ቀርቧል፡፡
“በኢትዮጵያ ውስጥ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አሟሟት ምስጢራዊ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ የተመረዘ ነገር ተሰጥቷቸው ነው የሞቱት ይባላል፡፡ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴም በተኙበት ነው ሞተው የተገኙት፡፡ የሰአሊና ገጣሚ አገኘሁ እንግዳ አሟሟትም ምስጢር ነው፡፡ ታዋቂው ድምፃዊ አሰፋ አባተም የተመረዘ ነገር ተሰጥቶት ነው የሞተው ይባላል፡፡ አቤ ጉበኛ እና በአሉ ግርማም ማን እንደገደላቸው እስከ አሁን ድረስ አልታወቀም፡፡ የጋዜጠኛ አሳምነው ገብረወልድ አማሟትም ምስጢር ነው፡፡”
የደራሲ ተመስገን ገብሬ አሟሟት ምን እንደሚመስል ግለ ታሪኩን በያዘው መፅሐፍ እውነተኛውን ምስል ማየት እንደተቻለው ሁሉ የደራሲ አቤ ጉበኛ “ብዕራዊ ተጋድሎ” በመፅሐፍ ተዘጋጅቶ በመቅረቡ አሟሟቱ ምን መልክ እንደነበረውና ከምን ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ፍርድና ትርጉሙን ለአንባቢያን ማቅረብ ተችሏል፡፡ እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ የሌሎቹም አሟሟት የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አንድ ቀን መገለፁ የማይቀር መሆኑን መፅሃፉ ይጠቁማል፡፡
በግል ጥላቻ፣ በጥቅም ግጭት በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት… አንዱ ለሌላው ውድቀትና ሞት መፍጠን ምክንያት የሆነበት ብዙ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ የክፋት ተግባር ፈፃሚዎቹ አሻራ ላለመተው ብርቱ ጥንቃቄ ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡ በጣም የሚገርመው አንዳንዶች በተዘጋጀላቸው ወጥመድ ተጠልፈው ሲወድቁ አንዳንዶች ተአምር በሚመስል መልኩ የተሸረበባቸው ተንኮል እንዳለ እንኳን ሳያውቁ ከአደጋ ይተርፋሉ፡፡
“የፈላስፎች ጉባኤ” መፅሐፍ መግቢያው ላይ ባሰፈረው ሃሳቡ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁን ጠልፎ ለመጣል የተደረገ ሴራና ከአደጋው ስለተረፉበት ታሪክ የቀረበ መረጃ አለ፡፡ ደራሲው በወቅቱ “ፍቅር እስከ መቃብር”ን አሳትመዋል፡፡ አንድ እወደድ ባይ፣ ንጉሥ ኃይለሥላሴ ዘንድ ይቀርብና “ጃንሆይ ይሄ ሀዲስ መንግሥታችንን አሳጣ፤ ምስጢር አወጣ፤ ገመናችንን ሁሉ በመፅሀፍ አሳትሞ አዋረደን!” ይላቸዋል፡፡
ንጉሡም እስኪ መፅሐፉን ልየው ይሉታል፡፡ አምጥቶ ሲያሳያቸው የፈጠራ ሥራ መሆኑን የዩና “ልቡ የወለደውን ነው የፃፈው፡፡ እኛን ምን አደረገንና ነው አዋረደን የምትለው?” በማለት ደራሲ ሀዲስ አለማየሁን ጠልፎ ለመጣል ያሰበውን ሰው አሳፍረው መለሱት፡፡ ንጉሡ የልወደድ ባዩን ማሳበቅ አምነው ተቀብለው ቢሆን ኖሮስ? ውጤቱን አለማሰቡ ነው የሚሻለው፡፡
ነገሥታት፣ አገልጋዮቻቸው፣ የፖለቲካ ሰዎች፣ በባለሙያነታቸው መታወቅና አንቱ መባል የሚፈልጉ አካላት፣ በጥቅም ተገናኝተው ለግጭት የሚዳረጉ ወገኖች… አርቀው እያሰቡ፣ እያመዛዘኑ፣ ሕሊናቸውን ተጠቅመው ካልተጓዙና ካልወሰኑ በአገርና ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳትና አደጋ ጥለው ያልፋሉ፡፡ በ2001 ዓ.ም በታተመው የደራሲ ተመስገን ገብሬ ግለ ታሪክ መፅሐፍ ላይ አሟሟታቸው አነጋጋሪ በመሆኑ ስማቸው የተነሳው ሰዎች ታሪክ ከሦስት ዓመት በኋላ በታተመው “የፈላስፎች ጉባኤ” ልቦለድ መፅሐፍ መግቢያ ተስፋፍቶ ቀርቧል - የነጋድራስ አፈወርቅ ገ/እየሱስና የደራሲ መንግሥቱ ገዳሙ ታክሎበት፡፡
የመፅሐፉ አዘጋጆች ይህንን ያደረጉበት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት “በርካታ ደራሲያን መፅሀፍቶቻቸውን የሚያሳትሙት እነዚህ ሰዎች በከፈሉት የህይወትና የደም ዋጋ ነው፡፡ የእነርሱን ውለታ ሳንጠቅስ ማለፍ” ስለከበደን ነው እንዳሉት ያልተገባ በደል የተፈፀመባቸው ሰዎች ወደፊትም ቢሆን ስማቸው ተደጋግሞ መነሳቱ አይቀርም፡፡

“የፈላስፎች ጉባኤ” በያዝነው ሳምንት ከማተሚያ ቤት ወጥቶ ለአንባቢያን የቀረበ መፅሐፍ ነው፡፡ በጋዜጠኝነታቸው የሚታወቁት የኤሚ እንግዳና የጥበቡ በለጠ 11 የልቦለድ ስብስቦችን የያዘው መፅሐፍ በመግቢያው “የስነ ፅሁፍን መስቀል ተሸክመው ለዚህያበቁንጠቢባንንአንዴእናስታውሳቸው” በሚል መነሻ እስከ ሞት ድረስ መስዋዕትነት የከፈሉ የኪነጥበብ ሰዎችን ያስተዋውቃል፡፡“ሕይወቴ (ግለ ታሪክ)” በሚል ርዕስ በ2001 ዓ.ም በታተመውና የደራሲ ተመስገን ገብሬን ህይወትና ሥራ በሚያስቃኘው መፅሐፍ ውስጥም በተመሳሳይ ሁኔታ በተቀነባበረ መልኩ ስለሞቱ የኪነ ጥበብ ሰዎች ይነገራል፡፡ በሁለቱም መፃህፍት ውስጥ በአንዱ በደራሲነት በሁለተኛው በአርታኢነት የተሳተፈው ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ ሰፋ ያለ ጥናት ያደረገ ይመስላል፡፡ የሆነ ሆኖ አሟሟታቸው ሚስጢር ስለሆነ 10 ያህል የኪነ ጥበብ ሰዎች ሁለቱ መፃህፍት መረጃውን ለአንባቢያን ማሸጋገሪያ ድልድይ ሆነዋል፡፡

“የጉለሌው ሰካራም” የሚል አጭር ልቦለድ ፅፎ በ1941 ዓ.ም ለአንባቢያን በማቅረቡ በዘርፉ ጀማሪ በመሆን ታሪክ የመዘገበው ደራሲ ተመስገን ገብሬ፤ ለሞቱ ምክንያት የሆነው ህመም መነሻው የተመረዘ ምግብ እንዲበላ በመደረጉ እንደሆነ ብዙ ሰዎች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ ደራሲ ተመስገን ገብሬ የተመረዘ ምግብ እንዲበላና እንዲሞት የተፈለገበት ምክንያት ምንድነው? በሚል ግለ ታሪኩን የያዘው መፅሐፍ ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል፡፡

ደራሲ ተመስገን ገብሬ በራሱ የሚተማመን ሰው ነበር፡፡ ለንጉሥ ኃይለሥላሴና ለቤተመንግሥታቸው የቅርብ ሰው ነው፡፡ የንጉሡን ልጆች ያስተምር ነበር፡፡ በጣሊያን ወረራ ወቅት በእንግሊዝ ለነበሩት አፄ ኃይለሥላሴ ደብዳቤ እየፃፈ በአገር ውስጥ ያለውን መረጃ ያቀብላቸዋል፡፡ ጠላት ከተባረረ በኋላ ሁሉም ንጉሡ ዘንድ እየቀረበ ሹመትና ሽልማት ሲጠይቅ ደራሲ ተመስገን ገብሬ የሚያስፈልኝን በራሴ ሰርቼ ማግኘት እችላለሁ ነበር ያለው፡፡ በአንዳንድ ጉዳይ ከባለስልጣናት ጋር ተከስሶ ይረታ ነበር፡፡ እነዚህ ጠንካራና ብርቱ ጐኖቹ ጠላት እንዲያፈራ ምክንያት ሆነውት ብቻ አልቀሩም፡፡ የተመረዘ ምግብ እንዲመገብ በስውር ተቀነባብሮ ሞቱ እንዲፋጠን ተደረገ፡፡

የደራሲ ተመስገን ገብሬን አሟሟት በሚተርከው ምዕራፍ ውስጥ ምክንያቱ በግልፅ በሚታወቅና በማይታወቅ አፈፃፀም በተቀነባበረ ዘዴሞትየተዳረጉ ናቸው በሚል የሚከተለው መረጃ ቀርቧል፡፡

“በኢትዮጵያ ውስጥ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አሟሟት ምስጢራዊ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለምሳሌ ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ የተመረዘ ነገር ተሰጥቷቸው ነው የሞቱት ይባላል፡፡ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴም በተኙበት ነው ሞተው የተገኙት፡፡ የሰአሊና ገጣሚ አገኘሁ እንግዳ አሟሟትም ምስጢር ነው፡፡ ታዋቂው ድምፃዊ አሰፋ አባተም የተመረዘ ነገር ተሰጥቶት ነው የሞተው ይባላል፡፡ አቤ ጉበኛ እና በአሉ ግርማም ማን እንደገደላቸው እስከ አሁን ድረስ አልታወቀም፡፡ የጋዜጠኛ አሳምነው ገብረወልድ አማሟትም ምስጢር ነው፡፡”

የደራሲ ተመስገን ገብሬ አሟሟት ምን እንደሚመስል ግለ ታሪኩን በያዘው መፅሐፍ እውነተኛውን ምስል ማየት እንደተቻለው ሁሉ የደራሲ አቤ ጉበኛ “ብዕራዊ ተጋድሎ” በመፅሐፍ ተዘጋጅቶ በመቅረቡ አሟሟቱ ምን መልክ እንደነበረውና ከምን ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ፍርድና ትርጉሙን ለአንባቢያን ማቅረብ ተችሏል፡፡ እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንዲሉ የሌሎቹም አሟሟት የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ አንድ ቀን መገለፁ የማይቀር መሆኑን መፅሃፉ ይጠቁማል፡፡

በግል ጥላቻ፣ በጥቅም ግጭት በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት… አንዱ ለሌላው ውድቀትና ሞት መፍጠን ምክንያት የሆነበት ብዙ አጋጣሚዎች አሉ፡፡ የክፋት ተግባር ፈፃሚዎቹ አሻራ ላለመተው ብርቱ ጥንቃቄ ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡ በጣም የሚገርመው አንዳንዶች በተዘጋጀላቸው ወጥመድ ተጠልፈው ሲወድቁ አንዳንዶች ተአምር በሚመስል መልኩ የተሸረበባቸው ተንኮል እንዳለ እንኳን ሳያውቁ ከአደጋ ይተርፋሉ፡፡

“የፈላስፎች ጉባኤ” መፅሐፍ መግቢያው ላይ ባሰፈረው ሃሳቡ ደራሲ ሀዲስ አለማየሁን ጠልፎ ለመጣል የተደረገ ሴራና ከአደጋው ስለተረፉበት ታሪክ የቀረበ መረጃ አለ፡፡ ደራሲው በወቅቱ “ፍቅር እስከ መቃብር”ን አሳትመዋል፡፡ አንድ እወደድ ባይ፣ ንጉሥ ኃይለሥላሴ ዘንድ ይቀርብና “ጃንሆይ ይሄ ሀዲስ መንግሥታችንን አሳጣ፤ ምስጢር አወጣ፤ ገመናችንን ሁሉ በመፅሀፍ አሳትሞ አዋረደን!” ይላቸዋል፡፡

ንጉሡም እስኪ መፅሐፉን ልየው ይሉታል፡፡ አምጥቶ ሲያሳያቸው የፈጠራ ሥራ መሆኑን የዩና “ልቡ የወለደውን ነው የፃፈው፡፡ እኛን ምን አደረገንና ነው አዋረደን የምትለው?” በማለት ደራሲ ሀዲስ አለማየሁን ጠልፎ ለመጣል ያሰበውን ሰው አሳፍረው መለሱት፡፡ ንጉሡ የልወደድ ባዩን ማሳበቅ አምነው ተቀብለው ቢሆን ኖሮስ? ውጤቱን አለማሰቡ ነው የሚሻለው፡፡

ነገሥታት፣ አገልጋዮቻቸው፣ የፖለቲካ ሰዎች፣ በባለሙያነታቸው መታወቅና አንቱ መባል የሚፈልጉ አካላት፣ በጥቅም ተገናኝተው ለግጭት የሚዳረጉ ወገኖች… አርቀው እያሰቡ፣ እያመዛዘኑ፣ ሕሊናቸውን ተጠቅመው ካልተጓዙና ካልወሰኑ በአገርና ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳትና አደጋ ጥለው ያልፋሉ፡፡ በ2001 ዓ.ም በታተመው የደራሲ ተመስገን ገብሬ ግለ ታሪክ መፅሐፍ ላይ አሟሟታቸው አነጋጋሪ በመሆኑ ስማቸው የተነሳው ሰዎች ታሪክ ከሦስት ዓመት በኋላ በታተመው “የፈላስፎች ጉባኤ” ልቦለድ መፅሐፍ መግቢያ ተስፋፍቶ ቀርቧል - የነጋድራስ አፈወርቅ ገ/እየሱስና የደራሲ መንግሥቱ ገዳሙ ታክሎበት፡፡

የመፅሐፉ አዘጋጆች ይህንን ያደረጉበት ምክንያት በአሁኑ ሰዓት “በርካታ ደራሲያን መፅሀፍቶቻቸውን የሚያሳትሙት እነዚህ ሰዎች በከፈሉት የህይወትና የደም ዋጋ ነው፡፡ የእነርሱን ውለታ ሳንጠቅስ ማለፍ” ስለከበደን ነው እንዳሉት ያልተገባ በደል የተፈፀመባቸው ሰዎች ወደፊትም ቢሆን ስማቸው ተደጋግሞ መነሳቱ አይቀርም፡፡

Read 3778 times