Print this page
Saturday, 21 January 2012 10:34

“ባለቤቴ ...ይናፍቀኝ ነበር”

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

እናቶች ከወሊድ በሁዋላ ከሚቸገሩባቸው ነገሮች አንዱ የመንፈስ ጭንቀት ወይንም የድብርት ስሜት ነው፡፡ ይህ ስሜት ሊመጣ የሚችለው በተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያው እንዲሁም ከኑሮ ጋር ተያያዥ በሆኑ የተለያዩ ምክንያቶች ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ሴቶች ከወለዱ በሁዋላ ልጆቻቸውን የመጥላት ባህርይ የሚያሳዩ ሲሆን በራሳቸውም ላይ ያልተለመዱ ሁኔታዎችን ያሳያሉ፡፡ ይህ ባህርይ በወሊድ ጊዜ ሲታይ ምናልባት ልጅ ከመውለድ ጋር በተያያዘ እንደትክክለኛ ነገር ሊወሰድ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በመውለድ ጊዜ ሊታይ የሚገባው መደሰት እንጂ መጨነቅ ዌንም መደበር ስላልሆነ የወለደችውን ሴት በቤተሰብ ደረጃ በተገቢው መንገድ ካልተንከባከቡአት እና ሁኔታው ብሶ ሲገኝም በህክምና ካልተረዳ ወደአእምሮ ችግር ሊለወጥ እንደሚችል ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ ምናልባትም ችግሩ ከወሊድ ጋር ተያይዞ ያልመጣ እና ቀደም ሲል ከነበረ የአእምሮ ችግር የሚነሳ ከሆነ በግልጽ ሊታይ የሚችልእና በቤት ውስጥ ሊታገሱት የማይችሉት ስለሚሆን በፍጥነት ወደሕክምና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ከወሊድ በሁዋላ የሚከሰት የአእምሮ ጭንቀት/ድብርት/ እስከአሁን በስፋት ለውይይት ያልቀረበ ስለሆነ ብዙ እናቶች የግል ችግር እንደሆነ አድርገው ሊቆጥሩት እንደሚችሉም  ዶ/ር አታላይ አለም የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዳይሬክተር እና የአእምሮ ሕክምና ባለሙያ አብራርተዋል፡፡ እንደ ዶ/ር አታላይ በሀገራችን ሁኔታው ያለበትን ደረጃ ለማወቅ የሚረዳ ጥናት የተደረገ ሲሆን ወደፊት በስፋት ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል ስራም ታቅዶአል፡፡ በዚህ እትም ወ/ሮ ሳራ በርሔ የተባለች እናት ልምድዋን አካፍላለች፡፡
----------------------------////-----------------------ኢሶግ የልጆች እናት ነሽ?
ወ/ሮ ሣራ አዎን፡፡የሶስት ልጆች እናት ነኝ፡፡
ኢሶግ ልጆችሽን በምትወልጅበት ጊዜ ስሜትሽ ምን ይመስል ነበር?
ወ/ሮ ሣራ አንዲት ሴት ልጅ በምትወልድበት ወቅት ከነበራት ሐሳብና ጭንቀት በመገላገልዋም ይሁን ልጅ በመውለድዋ ሊሰማት የሚገባት ስሜት የእፎይታ የደስታ መሆኑ የሚጠበቅ ነው፡፡ ነገር ግን ባለፈው እትማችሁ ያነጋገራችሁዋቸው ባለሙያም እንዳሉት እኔ በተለይም የመጀመሪያ ልጄን በወለድኩበት ጊዜ ልገልጸው የማልችለው የጭንቀት እና የድብርት ስሜት ነበረኝ፡፡
ኢሶግ ባህርይሽ እንዴት ሊገለጽ ይችል ይሆን ?
ወ/ሮ ሣራ ባህሪዬ እጅግ አስቸጋሪ ነበር ማለት እችላለሁ፡፡  ...ሆድ መባስ ...ማልቀስ... መበሳጨት...መጨነቅ...መከፋት... የመሳሰሉት ስሜቶች ይረብሹኝ ነበር፡፡ የምኖርበት ቤት ያስጠላኛል፡፡ ቤተሰቡ ማለትም አብረውኝ ያሉት ሰዎች ያስጠሉኛል፡፡ በእርግጥ ይህ ስሜት ሶስቱንም ልጆቼን ስወልድ የነበረ ቢሆንም የመጀመሪያው ጊዜ ግን በጣም የባሰ ስለነበር በጤናዬም ላይ የተለያዩ ችግሮችን አስከትሎብኝ ነበር፡፡
ኢሶግ የጤና ችግር ሲባል ምን አይነት ሕመም ደርሶብሽ ነበር?
ወ/ሮ ሣራ ማስታወክ ...ሆድ ቁርጠት...ተቅማጥ... የመሳሰሉት ሕመሞች ስለነበሩኝ ወደሐኪም ቤት እስከመሄድ ደርሻለሁ፡፡ በእርግጥ ይህ ችግር በመጀመሪያ ስወልድ እንደነበረው አልቀጠለም፡፡ ሌሎቹን ልጆች ስወልድ ከበፊቱ ልምድ በመውሰድ እራሴን ለማጽናናት እና እንደበፊቱ ወደከፋ የጤና ችግር እንዳልወድቅ ሞክሬአለሁ፡፡
ኢሶግ ከወለድሽ በሁዋላ የሚገጥምሽን ጭንቀት ወይንም ድብርት ባካባቢሽ ለነበሩ ሰዎች ገልጸሽላቸው ነበርን?
ወ/ሮ ሣራ እኔ ለማንም አልነገርኩም፡፡ የባህሪዬን ሁኔታና የእኔን መጨነቅ ማንም ያወቀ አይመስለኝም፡፡ ባለቤ ፣እና ፣እህቶቼ ፣የቤት ሰራተኞች ሁሉ በቤት ውስጥ በመገኘት እኔን ለማረስ ሽር ጉድ ሲሉ ይህንን የእኔን ችግር ግን አልተረዱትም፡፡ ማንም ሰው አልገባውም፡፡ እንኩዋንስ ቤተሰቤ እኔም እራሴ በትክክል ይህ ነው ብዬ መግለጽ አልቻልኩም ፡፡ ስለዚህ ብቻዬን ነበር ችግሩን የተቋቋምኩት፡፡
ኢሶግ ይህ ከወለድሽ በሁዋላ የነበረሽ ጭንቀት ወይንም ድብርት ለምን ያህል ጊዜ ቆይቶብሻል?
ወ/ሮ ሣራ በተለይም የመጀመሪያዋን ልጄን የወለድኩ ጊዜ ከአንድ ወር በላይ አሰቃይቶኛል፡፡ ሁኔታው አስከፊ ነበር፡፡ ልጄን ማጥባት አልፈልግም ፣ማንም እንዲያናግረኝ አልፈልግም ነበር፡፡ ሲያናግሩኝ የእኔ መልስ ቁጣ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ አብረውኝ ያሉ ሰዎች ግራ እስኪገባቸው ድረስ ተቸግሬአለሁ፡፡
ኢሶግ የችግሩን መንስኤ በምን መልክ ተረዳሽው ?
ወ/ሮ ሣራ ችግሩ ካለፈ በሁዋላ አንዳንድ መረጃዎች ስመለከት የገባኝ ነገር የምፈልገው ሰው በአቅራቢያዬ ስላልነበር ነው ብዬ አመንኩ፡፡ ከቤተሰቡ ሁሉ ባለቤን በጣም እወደው ስለነበር ይናፍቀኝ ነበር ፡፡ በእርግጥ ጠዋት ይወጣል ማታ ይገባል፡፡ ነገር ግን በትክክለኛው መንገድ ባለቤ ልጅ ወለደችልኝ ብሎ እንክብካቤ አላደረገልኝም፡፡ በቅርቤ አልተገኘም፡፡ ስለዚህ አብረውኝ ያሉት ሰዎች ሁሉ ምንም ቢያደርጉልኝ ልወዳቸው አልቻልኩም፡፡ያስጠሉኛል፡፡ ልክ እሱ ሲመጣ የነበረኝ ጭንቀት ሁሉ ይለቀኛል፡፡ ነገር ግን እቤቱ ከገባም በሁዋላ ወደእኔ ቀረብ ብሎ ማጽናናት ወይንም የደስታዬ ተካፋይ የመሆን ነገር ... ልጁን ታቅፎ የማየት ሁኔታ ስላልነበረው ተመልሼ በጣም አዝን ነበር፡፡ ነገር ግን ከወለድኩኝ ከሁለት ከሶስት አመት በሁዋላ አንድ ጥናት ሳነብ ሌሎችም የወለዱ ሰዎች እንደዚህ ያለ ችግር እንደሚደርስባቸው ሳውቅ በጣም ነበር የገረመኝ፡፡ ችግሩ አልጨከነም እንጂ ባስ ወዳለ የአእምሮ ሕመም ሊያመራም እንደሚችል ስገነዘብ ደግሞ በጣም ነው ያዘንኩት፡፡ ስለዚህ ሁኔታውን ለሌሎችም ማማከር ጀምሬአለሁ፡፡
ኢሶግ ከወለድሽ በሁዋላ ችግሩ እንዲቀረፍ በራስሽ የወሰድሽው እርምጃ ነበር?
ወ/ሮ ሣራ የመጀመሪያ ልጄን ስወልድ የነበረው የመንፈስ ጭንቀት ከጭንቀትም አልፎ ሌላ የጤና ችግር እስከማስከተል የደረሰ በመሆኑ በህክምና ነው እራሴን ያረጋጋሁት፡፡ ነገር ግን ሁለተኛና ሶስተኛ ልጅ ስወልድ የነበረኝ የመንፈስ ጭንቀት ምን እንደሆነ ስለተረዳሁት በተቻለኝ መጠን እራሴን ለማረጋጋት ሞክሬ አለሁ፡፡ ለቤተሰቤም ሁኔታውን እያስረዳሁ እንዲታገሱኝና ባህሪዬን እንዲያውቁልኝ ለማድረግ ሞክሬአለሁ፡፡ ...ለምሳሌ አልበላም ወይንም አልጠጣም ስል እንዲተውኝ...መተኛት ስፈልግ እረፍት እንዳይነሱኝ....ማንኛውንም ነገር እኔን እንዲመቸኝ አድርገው እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ እየሞከርኩ በተሻለ ሁኔታ ችግሩን ለማስተናገድ ሞክሬአለሁ፡፡
ኢሶግ የባልተቤትሽ ሁኔታስ?
ወ/ሮ ሣራ የእኔ ባለቤት ሁኔታ ምንም አልተሸሻለም፡፡ እኔ ግን በተቻለኝ መጠን እሱ ሊያደርግልኝ ይገባል... የሚለውን ስሜን ወደጎን በመተው ወደ እራሴ እና ወደ ልጄ በማዘንበል ችግሩን ለመቅረፍ ሞክሬአለሁ፡፡ ትልቁን ምክር መስጠት የምፈልገው ለባሎች ነው፡፡ ከእኔ ጉዳይ ስነሳ ባሎች አባቶች ሚስቶቻቸው ሲወልዱ ትልቁን ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡ ባሎች ...ሚስቶቻቸው ሲወልዱ ጊዜ ሰጥተው እቤት ውስጥ በመገኘት... ባለቤቱ በመውለዱዋ አመስግኖ ...ሸልሞ ... ወዘተ ...እናትየውን የሚያስደስት ነገር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ እናትየው ልጅ በመውለድዋ ምክንያት ባልዋ የሰጠውን ክብደት በማየት... ለእርስዋ ያለውን ፍቅር የምታረጋግጥበት ወቅት በመሆኑ ከወለደች በሁዋላ ለሚፈጠረው የመንፈስ ጭንቀት አትጋለጥም፡፡ ስለዚህ ሚስት በምትወልድበት ጊዜ ባልየው በተቻለ መጠን በቅርብዋ መገኘት ...ምን በላች... ምን ጠጣች...እስከሚለው ድረስ ቢንከባከባት... ሚስት በጣም ስለምትደሰት ለአእምሮ ጭንቀት ወይንም ድብርት አትጋለጥም ብዬ አስባለሁ፡፡ በእኔ ላይ የደረሰው ከመውለድ በሁዋላ የአእምሮ ጭንቀት ምክንያቱ ባለቤ ለእኔ ተገቢውን ድጋፍ አለማድረጉ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
-------------------------////-----------------------
አንዲት እናት ከወለደች በሁዋላ የመንፈስ ጭንቀት ቢያድርባት ወይንም በአእምሮዋ የጤና ችግር ቢደርስባት ወደሐኪም ለመቅረብ ልታደርገው የሚገባት ...
ከወትሮው ባህርይዋ የተለየ የሚመስላትን ነገር እና ለምን ያህል ጊዜሰአት ሁኔታው እንደቆየ መመዝገብ፣
ወደህክምናው አገልግሎት በምትሄድበት ጊዜ ቀደም ሲል የነበራራትን የህክምና መረጃ መዝግቦ መያዝ፣ ምናልባትም ከእርግዝናው ክትትል ውጭም የአእምሮ ወይንም ሌላ የአካል ጤንነቶችን በሚመለከት የተደረገ ምርመራራ ካለ ማስታወስ፣
የሚያምኑትን ወይንም የሚቀርቡትን ቤተሰብ ወይንም ጉዋደኛ በመምረጥ በህክምና ቀጠሮ ላይ እንዲገኝ ማድረግ...የዚህም ምክንያቱ የተነገረውን ነገር ሁሉ ማስታወስ ቢያቅት እንኩዋን አብሮ የነበረ ሰው ሊያስታውስ ስለሚችል ነው፡፡
ወደሐኪም የሚቀርበውን ጥያቄ አስቀድሞውኑ መዝግቦ መያዝ ይጠቅማል፡፡
Postpartum depression  ከወሊድ በሁዋላ የሚደርስ የመንፈስ ጭንቀት ወይንም ድብርት ብዙውን ጊዜ የህክምና ድጋፍ ሳይፈልግ የሚድን ሲሆን አልፎ አልፎ ግን ወደህክምና ሊያስኬድ የሚችል ባህርይ አለው፡፡ ከዚህ ውጭ ግን ችግሩ ሲፈጠር...
በስነአእምሮ ወይንም ተመሳሳይ ሙያ ባለቸው የህክምና ባለሙያዎች የምክር አገልግሎት ማግኘት፣
በሕክምና ባለሙያዎች የሚታዘዙ መድሀኒቶችን መውሰድ፣
ኢስትሮጂን የተባለውን ሆርሞን መተካት ለአንዳንድ ሴቶች ከወሊድ በሁዋላ መደበር ወይንም ጭንቀት ምክንያቱ የኢስትሮጂን እጥረት ስለሚሆን በሕክምና ባለሙያ በሚሰጥ ትእዛዝ መሰረት ሆርሞኑን መተካት...)
ESOG – Ethiopian Society of Obsettricians and Gynacologists የኢትዮጵያ ፅንስና ማህፀን ሃኪሞች ማህበር ማለት ሲሆን ይህንን አምድ
ከአድማስ አድቨርታይዚንግ ጋር በመተባበር የሚያቀርብላችሁ ድርጅት ነው፡፡ (በፖ.ሣ.ቁ 8731 ስልክ 011-5-506068/69 ልታገኙን ትችላላችሁ)

Read 5498 times