ሮበርት ፍሮስት
አሜሪካዊ ገጣሚ
የታሪክ ባለሙያ ማለት ያለፈውን ዘመን መተንበይ የሚችል ነቢይ ነው፡፡
ፍሬድሪክ ቮን ሽሌግል
ጀርመናዊ ሃያሲና ፈላስፋ
የዊንስተን ቸርችልን ሱሪ ለመልበስ እየሞከረች ነው፡፡
ሊኦኒድ ብሬዥኔቭ
የሶቭየት ፕሬዚዳንት የነበሩ
(ስለማርጋሬት ታቸር የተናገሩት)
ህዝብ የራሱን ታሪክ ስሜታዊ ሳይሆን ለመመልከት ፈቃደኛ መሆን አለበት፡፡
ዊሊ ብራንድት
የጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣን የነበረ
(የሁለተኛው ዓለም ጣርነት 25ኛ ዓመት ሲዘከር የተናገሩት)
የምረጡኝ ዘመቻውን በቅጡ እንደመራው ሁሉ አገሪቱንም በቅጡ ቢመራ ደህና እንሆን ነበር፡፡
ዳን ኩያሌ
አሜሪካዊ ፖለቲከኛ
(እ.ኤ.አ በ1992 የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከተሸነፉ በኋላ ስለ ክሊንተን የተናገሩት)
ሂትለር የእኛን ሃሳብ ወስዶ አብዮት በማካሄዱ ደስተኛ ልሆን ይገባል ብዬ አስባለሁ፡፡ ችግሩ ግን ጀርመኖች ናቸውና የማታ ማታ ሃሳባችንን ማበላሸታቸው አይቀርም፡፡
ቤኒቶ ሙሶሎኒ
ጣሊያናዊ አምባገነን መሪ የነበረ
(የተለየ የጣልያናውያን ፍልስፍና አድርጐ የሚቆጥረውን ፋሺዝም በተመለከተ የተናገረው)
ሦስተኛው ዓለም እውነታ አይደለም፤ ርዕዮተ ዓለም እንጂ፡፡
ሃና አሬንድት
(ትውልደ ጀርመን አሜሪካዊት ፈላስፋና የታሪክ ምሁር)
ማንም ነፃ ሰው የጦር መሳሪያ ከመታጠቅ ሊገደብ አይገባም፡፡ ህዝብ የጦር መሳሪያ የመያዝና የመታጠቅ መብቱ መጠበቅ የሚኖርበት ዋናው ምክንያት እንደ መጨረሻ አማራጭ ራሱን ከጨቋኝ መንግስት እንዲከላከል ነው፡፡
ቶማስ ጀፈርሰን
(የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩ)
ፋሺዝም ለውጭ አገር ገበያ የሚላክ እቃ አይደለም፡፡
ቤኒቶ ሙሶሎኒ
(በጀርመን ፕሬስ የተዘገበ)