Monday, 02 March 2015 09:47

የብጉር ችግሮችና መፍትሔዎቹ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(29 votes)

ብጉር በአብዛኛው በወጣትነት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ላይ በስፋት የሚታይ የፊት ቆዳ ችግር ነው፡፡ የብጉር ችግር በብዛት ዕድሜያቸው ከሃምሳ አምስት በላይ በሆኑ ሰዎች ላይ አይታይም፡፡ ይሁን እንጂ በወጣትነት ዕድሜያቸው ላይ የጀመራቸው የብጉር ችግር ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድም ላይቀረፍ የሚችልባቸው አጋጣሚዎች ይኖራሉ፡፡
ብጉር በፊት ላይ የሚወጡ ሽፍታና ከፍ ከፍ ያሉ እባጭ አይነት ነገሮች መጠሪያ ሲሆን እነዚህ ሽፍታዎችና እባጮች አንዳንድ ጊዜም ከፊት በተጨማሪ በደረትና ጀርባ ላይ ሊወጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ እባጭ ነገሮች አንዳንድ ጊዜ እየተገጣጠሙ ይፈነዱና በፊት ላይ፣ በደረትና ጀርባ ላይ ቁስለት ሊፈጥሩና ውበትንም ሊያበላሹ ይችላሉ፡፡

የብጉር መንስኤዎች
በፊታችን፣ በደረትና በጀርባችን ቆዳዎች ላይ ከአስፈላጊ መጠን በላይ የሆነ ቅባት ሲከማችና ወዝ ሲፈጠር የቆዳችን ጥቃቅን ቀዳዳዎች ይደፈናሉ፡፡ በዚህ ጊዜም በቆዳችን ቀዳዳ መውጣት የሚገባው ቆሻሻ መውጣት ስለማይችል በቆዳችን ላይ እብጠት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቆዳችን ላይ ያለው Propion pbactrium acnes የተባለ ባክቴሪያ ቆዳውን እንዲቆጣና እብጠት እንዲከሰት ያደርገዋል፡፡
ብጉርን ለመቀነስ
ምን ማድረግ ይገባል?
በሞቀ ውሃና በሳሙና ፊትን በየጊዜው መታጠብ፣
ለዚህ ችግር ተብለው የተሰሩ መድሀኒቶችን፣ መታጠቢያዎችንና ቅባቶችን መጠቀም፣
የህክምና ባለሙያዎችን ማነጋገርና መፍትሄ መፈለግ፣

Read 15639 times