Print this page
Monday, 02 March 2015 09:47

የእንቅልፍ እውነታዎች

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(3 votes)

የእንቅልፍ እውነታዎች
አንድ ሰው ከህይወት ዘመኑ አንድ ሶስተኛ ጊዜውን ለእንቅልፍ ያውላል፡፡
70% የሚሆኑና ለጤንነታችን እጅግ አስፈላጊ የሆኑ ሆርሞኖች በእንቅልፍ ሰዓት ራሳቸውን በሃይል ይሞላሉ፡፡
በየቀኑ ከ7 ሰዓታት በታች የሚተኛ ሰው ድብርት፣ ጭንቀት፣ ውጥረት፣ የደም ግፊት፣ ስኳር፣ ለልብና የመገጣጠሚያ ህመሞች እንዲሁም ለአስም በሽታ የመሃለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡
በአሜሪካ ውስጥ ከሚኖሩ ህዝቦች ወደ 60 በመቶ የሚጠጉት ስር በሰደደ የእንቅልፍ ችግር የተጠቁ ናቸው፡፡
በአሜሪካ ከእንቅልፍ ማጣት ችግር ጋር በተያያዘ የሚደርሱ አደጋዎች በአራተኛ ደረጃ በገዳይነት የተፈረጁ ሲሆን በመኪና አደጋ ከሚደርሰው ሞት ውስጥ 51 በመቶ የሚሆነው በእንቅልፍ ማጣት ምክንያት የሚከሰት ነው፡፡

Read 3812 times