ዛዛ ጋቦር
(ትውልደ ሃንጋሪ አሜሪካዊ የፊልም ተዋናይ)
እያፈቀሩ ብልጥ መሆን አይቻልም፡፡
ፍራንሲስ ቤከን
(እንግሊዛዊ ፈላስፋ፣ ፖለቲከኛና ጠበቃ)
አንዲት ሴት በህይወት ዘመኗ አንዴ ወይም ሁለቴ መጥፎ ወንድ ማፍቀር አለባት - አመለ ቀናውን እንድታመሰግን፡፡
ማጆሪ ራውሊንግስ
(አሜሪካዊ የረዥም ልብወለድ ደራሲ)
ሴት ልጅ የሚያፈቅራትን ወንድ እንጂ የምታፈቅረውን ወንድ ማግባት የለባትም፡፡ ያ ነው የዘላቂ ደስታ ምስጢሩ፡፡
ማርያማ ባ
(ሴኔጋላዊት ደራሲና የሴቶች መብት ተሟጋች)
የሴት ልብ ሁልጊዜ የቃጠሎ ምልክት አለበት፡፡
ሉዊስ ላቤ
(ፈረንሳዊ ገጣሚ)
መኖር አልፈልግም - መጀመርያ ማፍቀር ነው የምሻው፡፡ ከዛም እግረ መንገዴን ብኖር አልጠላም፡፡
ዜልግ ፊትዝገራልድ
(አሜሪካዊ ፀሐፊ)
እያንዳንዱ ወንድ የሚኖረው ለራሱ በሚያደርገው እን
ክብካቤ ሳይሆን በፍቅር እንደሆነ ተገንዝቤአለሁ፡፡
ሊዮ ቶልስቶይ
(ሩሲያዊ ደራሲ)
ስትስመኝ ነበር የተወለድኩት፡፡ በህይወት የኖርኩትም ስታፈቅረኝ በነበረበት ጥቂት ሳምንታት ያህል ነው፡፡ ትታኝ ስትሄድ ሞትኩኝ፡፡
ሃምፍሬይ ቦጋርት
(አሜሪካዊ አክተር)