Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 January 2012 11:50

የአፄ ቴዎድሮስ ሐውልት በጎንደር ይመረቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ዘመናዊቷን ኢትዮጵያ በመመስረት ትልቅ የጀማሪነት ድርሻ የነበራቸው የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ፋይበር ግላስ ሃውልት በጎንደር ከተማ ፒያሳ አደባባይ በመጪው ረቡዕ ይመረቃል፡፡ ቀራፂ ብዙነህ ተስፋ የቀረፀውን ሐውልት ያሰራው የጎንደር ከተማ አስተዳደር እንደሆነ ታውቋል፡፡ ሐውልቱ የልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ እና የሴባስቶፖል መድፍ በተለጣፊነት ይኖሩታል፡፡ ይኸው ሐውልት ወደ ጎንደር እየተጓጓዘ ሲሆን በጥምቀት ዋዜማ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ በሚገኙበት ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ለጊዜው አደባባይ ላይ የሚቆመው ሐውልቱ ብቻ ሲሆን የሕዝብ ቤተመፃሕፍት በሥፍራው ለማቋቋም በእለቱ የመሠረት ድንጋይ ይጣላል፡፡ በኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል ወቅት የአፄ ቴዎድሮስን ሐውልት ለማቆም ታቅዶ እንደነበርና ሳይሳካ በመቅረቱ ህዝቡ ቅር ተሰኝቶ እንደነበር ታውቋል፡፡

ሐውልቱ የተሰራው በዓለም ባንክ እና በአስተዳደሩ የጋራ በጀት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

 

 

Read 2132 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 11:53