Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 14 January 2012 11:47

ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ስለፊልም ገለፃ ያደርጋሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በፈረስ ዙሪያ እና “This is Workneh Bezu” የሥዕል አውደርእዮች ተከፈተ

የፊልም ባለሙያው ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ በፊልም ዙሪያ ለወጣት ባለሙያዎች ትምህርታዊ ገለፃ እንደሚያደርጉ “ሲኔ ክለብ ደ አዲስ” የተሰኘው የፊልም ክለብ አስታወቀ፡፡ በመጪው ማክሰኞ ከቀኑ 11 ሰዓት ፒያሳ በሚገኘው አሊያንስ ኢትዮ ፍራንስ የሚጀመረው ትምህርታዊ ዝግጅት በሳምንቱ ታህሣሥ 15 ቀን 2004 ዓ.ም እንደሚቀጥልም ከፊልም ክለቡ መረዳት ተችሏል፡፡

በሌላ በኩል ጭብጡን በፈረስ ዙሪያ ያደረገና ርእስ ያልተሰጠው የሥእል አውደርእይ በአሊያንስ ኢትዮ-ፍራንስ ባለፈው ሰኞ እንደተከፈተ ለማወቅ ተችሏል፡፡ እስከ ጥር 18 ቀን 2004 ዓ.ም በሚቆየው በዚሁ አውደርእይ የሠዓሊ ሙሉ ቀን ደበበ 23 ፈረስ ነክ የቀለም ቅብ ሥራዎችና 6 የንድፍ ሥራዎች ቀርበዋል፡፡ ሠዐሊው ካሁን ቀደም በርካታ ጊዜ በቡድን አውደርእይ ያቀረበ ሲሆን ለብቻው ሲያቀርብ ግን ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ በሌላም በኩል 80 ያህል የወርቅነህ በዙ ሥራዎችን ያካተተ የስዕል አውደርዕይ በአበሻ አርት ስቱዲዮና አዲስ ምዕራፍ ፕሮሞሽን ትናንት ተከፈተ፡፡

 

 

 

Read 2387 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 11:49