Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 14 January 2012 11:25

ቢዮንሴ ሴት ልጅ በአጀብ ተገላገለች ጄይዚ ለልጁ መታሰቢያ ነጠላ አልበም ለቀቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የ30 ዓመቷ አሜሪካዊት አቀንቃኝ ቢዮንሴ ጂዜል ኖውልስ የመጀመሪያ ሴት ልጇን በተጠናከረ ጥበቃና በከፍተኛ ወጪ በሰላም የተገላገለች ሲሆን ህፃኗ ብሉ አይቪ ካርተር የሚል ስም ወጥቶላታል፡፡ ኤም ቲቪ ኒውስ እንደዘገበው የህፃኗ ስም የወጣላት ቢዮንሴና ፍቅረኛዋ የሰሯቸው አልበሞች መጠርያዎች መነሻ በማድረግ ነው፡፡ የቢዮንሴ ፍቅረኛና የህፃኗ አባት ራፐሩ ጄይዙ ለልጁ መታሰቢያ የሚሆን ነጠላ ዜማ ህፃኗ በተወለደች ማግስት እንደለቀቀ የታወቀ ሲሆን የዜማውን ስያሜም “ግሎሪ ፊት ቢ.አይ.ሲ” ብሎታል፡፡

ድምፃዊቷ የእርግዝና ወቅት ቤተሰቧ በተለያዩ አሉባልታዎች ሲታመሱ እንደከረሙ ያመለከቱ ዘገባዎች፤ ጽንሱ የውሸት ነው፣ ተጨናግፏል፣ ከወር በፊት ተወልዷልና መሰል ወሬዎች ሲናፈሱ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡ የደስታ መግለጫ ለጥንዶቹ በቀዳሚነት ከላኩ አርቲስቶች አንዷ የሆነችው የቅርብ ወዳጃቸው ሪሃና ህፃኗን “ልዕልት ካርተር” እንዳለቻት ተዘግቧል፡፡ የሴት ልጅ እናት ለመሆን የበቃችው ቢዮንሴ ከአራስ ቤት እንደወጣች አዲስ አልበም የመስራትና በመላው ዓለም ኮንሰርቶች የማቅረብ ዕቅድ እንዳላት የተዘገበ ሲሆን ከጄይዚ ጋርም አንድ የጋራ አልበም ሊያወጡ ይችላሉ ተብሏል፡፡

 

 

 

 

Read 4911 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 11:45

Latest from