Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 14 January 2012 11:15

የሆሊዉድ ፊልም ሰሪዎች ከሽልማት ይልቅ ለገበያ ትኩረት ሰጥተዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ቀደም ባሉት ጊዜያት የሆሊዉድ ፊልም ሰሪዎች ለታላላቆቹ የኦስካርና የጐልደን ግሎብ ሽልማቶች ከፍተኛ ትኩረት ይሰጡ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ቀልባቸው ከሽልማት ይልቅ አለምአቀፍ ገበያ ላይ እንዳረፈ “ዘ ሆሊዉድ ሪፖርተር” ዘግቧል፡፡ ከሰሜን አሜሪካ ውጭ የሆሊዉድ ፊልሞች በቻይና በብራዚልና በሩሲያ ከፍተኛ ተፈላጊነትና ገበያ እንዳላቸውም ታውቋል፡፡ የሩሲያ የፊልም ኢንዱስትሪ በአብዛኛው ወጣትና ታዳጊ የፊልም ተመልካቾች የያዘ እንደሆነ የጠቆመው “ዘ ሆሊዉድ ሪፖርተር”፤ በዓመት እስከ 150 ሚሊዮን የሚደርሱ ትኬቶች እንደሚሸጡ አመልክቷል፡፡

በየዓመቱ 20 የውጭ አገር ፊልሞችን እየተቀበለ የሚያስተናግደው የቻይና የፊልም ኢንዱስትሪም ፈጣን ዕድገት እያሳየ ሲሆን በየዓመቱ እስከ 1.5 ቢ. ዶላር የሚደርስ ገቢ ለሆሊዉድ የፊልም ስቱዲዮዎች ያስገባል፡፡ በሌላ በኩል ከ10 ዓመት በላይ የኦስካር ሸልማት ስነስርዓት ሲካሄድበት የቆየውና የዘንድሮም የሚካሄድበት የኮዳክ ትያትር አዳራሽ ከቀጣዩ ዓመት በኋላ ይሄንን ዕድል ላያገኝ እንደሚችል “ሎስ አንጀለስ ታይምስ” ዘገበ፡፡ የትያትር አዳራሹ ከኦስካር አዘጋጅ ከአካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ምሽን ፒክቸርስ ጋር ለ20 ዓመት የሚቆይ ውል የነበራቸው ቢሆንም ከ2013 በኋላ ውሉ ሊፈርስ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ የኮዳክ ትያትር አዳራሽ በአንድ ጊዜ 3332 እንግዶችን መያዝ የሚችል ሲሆን በየዓመቱ በሚካሄደው የኦስካር ስነስርዓት 6.9 ሚ ዶላር ገቢ እንደነበረው ሎስ አንጀለስ ታይምስ ጠቁሟል፡፡ የኦስካር አዘጋጁ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ምሽን ፒክቸርስ ከኮዳክ ጋር ውሉን ለማቋረጥ የፈለገው የአሜካን አይዶል የፍፃሜ ውድድርን ባስተናገረደውና የበለጠ እንግዶችን በሚይዘው የኖኪያ ትያትር አዳራሽ ለመጠቀም በማቀዱ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የኖኪያ ትያትር አዳራሽ 7100 ተመልካቾችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ይችላል፡፡

 

 

 

Read 1639 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 11:16

Latest from