በየዓመቱ 20 የውጭ አገር ፊልሞችን እየተቀበለ የሚያስተናግደው የቻይና የፊልም ኢንዱስትሪም ፈጣን ዕድገት እያሳየ ሲሆን በየዓመቱ እስከ 1.5 ቢ. ዶላር የሚደርስ ገቢ ለሆሊዉድ የፊልም ስቱዲዮዎች ያስገባል፡፡ በሌላ በኩል ከ10 ዓመት በላይ የኦስካር ሸልማት ስነስርዓት ሲካሄድበት የቆየውና የዘንድሮም የሚካሄድበት የኮዳክ ትያትር አዳራሽ ከቀጣዩ ዓመት በኋላ ይሄንን ዕድል ላያገኝ እንደሚችል “ሎስ አንጀለስ ታይምስ” ዘገበ፡፡ የትያትር አዳራሹ ከኦስካር አዘጋጅ ከአካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ምሽን ፒክቸርስ ጋር ለ20 ዓመት የሚቆይ ውል የነበራቸው ቢሆንም ከ2013 በኋላ ውሉ ሊፈርስ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ የኮዳክ ትያትር አዳራሽ በአንድ ጊዜ 3332 እንግዶችን መያዝ የሚችል ሲሆን በየዓመቱ በሚካሄደው የኦስካር ስነስርዓት 6.9 ሚ ዶላር ገቢ እንደነበረው ሎስ አንጀለስ ታይምስ ጠቁሟል፡፡ የኦስካር አዘጋጁ አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ኤንድ ምሽን ፒክቸርስ ከኮዳክ ጋር ውሉን ለማቋረጥ የፈለገው የአሜካን አይዶል የፍፃሜ ውድድርን ባስተናገረደውና የበለጠ እንግዶችን በሚይዘው የኖኪያ ትያትር አዳራሽ ለመጠቀም በማቀዱ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የኖኪያ ትያትር አዳራሽ 7100 ተመልካቾችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ ይችላል፡፡