Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 14 January 2012 11:11

ሆረር ፊልሞች ወደ ሲኒማ ገበያው መጥተዋል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በተለያዩ አስፈሪ ጭብጦች የተሰሩ ፊልሞች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ገበያውን ማጥለቅለቅ መጀመራቸውንና በገቢም ስኬታማ ይሆናሉ ተብለው እንደሚገመቱ ቦክስ ኦፊስ ሞጆ አመለከተ፡፡ ብዙዎቹ የሆረር ፊልሞች በሃይማኖታዊ ጉዳዮችና በውስብስብ የስነልቦና ችግሮች ላይ ያተኩራሉ፡፡ ባለፈው ሳምንት በ2285 ሲኒማዎች ለእይታ የበቃው እጅግ አስፈሪ ሆረር ፊልም “ዘ ዴቭል ኢንሳይድ” በመጀመርያ ሳምንቱ 33.7 ሚሊዮን ዶላር በማስገባት የቦክስ ኦፊስ ሳምንታዊ የገቢ ደረጃን መሪነት ተቆጣጥሯል፡፡

የ “ዘ ዴቭል ኢንሳይድ”  የመጀመርያ ሳምንት ገቢ በቦክስ ኦፊስ ታሪክ 3ኛው ከፍተኛ ሳምንታዊ ገቢ ሆኖም ተመዝግቧል፡፡በሰሜን አሜሪካ የፊልም ገበያ በ2012 ሁለተኛ ሳምንት ላይ የተመልካች ብዛት በ59 በመቶ ማደጉን ያወሳው “ዘ ሆሊውድ ኒውስ” በበኩሉ፤ በፓራማውንት ፒክቸርስ የተሰራው “ዘ ዴቪል ኢንሳይድ” ለእይታ ከመብቃቱ በፊት በገበያ ትውውቅ ጥሩ መንቀሳቀሱ ሳምንታዊ ገቢውን እንዳሳደገው አመልክቷል፡፡

 

 

Read 1991 times Last modified on Saturday, 14 January 2012 11:14

Latest from