Saturday, 31 January 2015 12:32

ሃና ላላንጎን አስገድደው በመድፈር ለሞት ዳርገዋል የተባሉት ተጠርጣሪዎች እንዲከላከሉ ተወሰነ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(8 votes)

ከወራት በፊት የ15 ዓመቷን ታዳጊ ሃና ላላንጎን ከት/ቤት ስትመለስ በታክሲ አሳፍረው በመውሰድና በተደጋጋሚ አስገድደው በመድፈር ለሞት ዳርገዋል በሚል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው አምስት ወጣቶች እንዲከላከሉ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈው ረቡዕ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
በከባድ የሰው ግድያና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የተከሰሱት አምስቱ ወጣቶች ላይ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን አሰምቶ የጨረሰ ሲሆን ፍ/ቤቱ የምስክሮችን ቃልና ክሱን መርምሮ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ይዞ ነበር፡፡  ባለፈው ረቡዕም ፍ/ቤቱ ተጠርጣሪዎቹ ወጣቶች ክሱን እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ሲሆን መከላከያቸውን ለመስማትም ለፊታችን አርብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Read 6003 times