Monday, 05 January 2015 08:40

2014 አመቱን በቁጥር

Written by 
Rate this item
(2 votes)

55 በመቶ
ስኮትላንድ ከእንግሊዝ ተገንጥላ ራሷን ለመቻል ባካሄደችው ሪፈረንደም ከእንግሊዝ ጋር ብንቆይ ይሻላል ሲሉ ድምጻቸውን የሰጡ ስኮትላንዳውያን፡፡
3 ሺህ 400
በአመቱ ወደተለያዩ የአውሮፓ አገራት ለመግባት ሲሞክሩ በሜዲትራኒያን ባህር ሰጥመው የሞቱ ስደተኞች ቁጥር፡፡
529
በመጋቢት ወር በግብጽ ውስጥ በተካሄደ የፍርድ ሂደት የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ ሙርሲ ደጋፊዎች፡፡

17.6 ትሪሊዮን ዶላር
በአመቱ የቻይና ኢኮኖሚ ከአሜሪካ በመብለጥ በአለማችን ቀዳሚነቱን የያዘበት፡፡

51 ቢሊዮን ዶላር
በኦሎምፒክ ታሪክ ከፍተኛ ወጪ እንደወጣበት የተነገረውና በአመቱ በሩስያ የተካሄደው የ2014 የሱሺ የዊንተር ኦሎምፒክ ውድድር አጠቃላይ ወጪ፡፡

44.4 ሚሊዮን ዶላር
ጂምሰን ዊድ/ ዋይት ፍላወር 1 የተሰኘውና በሴት ሰኣሊያን ከተሰሩ የስዕል ስራዎች በከፍተኛ ገንዘብ በመሸጥ ክብረወሰን ያስመዘገበው የሰዓሊ ጂዮርጂያ ኦኬፌ የስዕል ስራ ባለፈው ህዳር ወር የተሸጠበት ዋጋ፡፡

3 ሺህ
በሶርያና በኢራቅ የሚንቀሳቀሱ አክራሪ እስላማዊ ቡድኖችን በ2014 የተቀላቀሉ አውሮፓውያን ቁጥር፡፡

10 ሚሊዮን
ታዋቂው የቴክኖሎጂ ኩባንያ አፕል ባለፈው መስከረም ወር ለገበያ ያቀረባቸው አይፎን6 እና አይፎን6 ፕላስ ዘመናዊ የሞባይል ቀፎዎች በአንድ ሳምንት ጊዜ የተሸጡበት ቁጥር፡፡

7ሺህ 857
የዓለም የጤና ድርጅት እስከዚህ ሳምንት ድረስ በኢቦላ ሳቢያ ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል ያላቸው ሰዎች ቁጥር፡፡
61 ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች
የእንግሊዝ ብሄራዊ የስታስቲክስ ቢሮ መረጃ እንደሚለው በአገሪቱ በሴተኛ አዳሪነት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሴቶች ቁጥር በተጠናቀቀው የፈረንጆች አመት 61 ሺህ ደርሷል፡፡
አንድ ሴተኛ አዳሪ ለአንድ ጊዜ ወሲባዊ ግንኙነት የምታስከፍለው ገንዘብ በ2014 በአማካይ 67 ፓውንድ መድረሱን የጠቆመው መረጃው፣ አንዲት ሴተኛ አዳሪ በሳምንት በአማካይ ከ23 ወንዶች ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ትፈጽማለች ብሏል፡፡
814 ሚሊዮን
በታሪክ በርካታ ዜጎች ድምጽ የሰጡበት ቀዳሚው የፖለቲካ ምርጫ በተባለውና ባለፈው ሚያዝያ ወር በተከናወነው የህንድ ምርጫ ድምጽ የሰጡ የአገሪቱ ዜጎች ቁጥር፡፡
9223372036854775808 ወይም 9 ኩንቲሊዮን
ደቡብ ኮርያዊው ድምጻዊ ፒኤስዋይ ከሁለት አመታት በፊት የለቀቀው ጋንጋም ስታይል የተሰኘ የሙዚቃ ክሊፕ በዩቲዩብ ድረገጽ የታየበት ቁጥር፡፡
(ምንጭ፡- ፋይናንሺያል ታይምስና ሌሎች ድረገጾች)

Read 2019 times