በጋዜጠኛ ሃብታሙ ስዩም የተፃፈው “ማሳቅ፣ ማሳዘን፣ ማሸበር” የተሰኘ መፅሀፍ ገበያ ላይ ዋለ፡፡ የመፅሀፉ ይዘት ፖለቲካዊ ቧልት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ 20 ያህል ታሪኮችን የያዘውና በ176 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ49 ብር ይሸጣል፡፡ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ስዩም ከዚህ ቀደም “አስራ ሰባት መርፌና ሃያ ምናምን ቁምጣ” የተሰኘ የወግ መፅሀፍ ለአንባብያን ማድረሱ ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት በስደት ላይ የሚገኘው ሃብታሙ ስዩም፤ በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬዲዮ የሸገር ሼልፍ ፕሮግራም አዘጋጅ፣ በኋላም የ“አዲስ ጉዳይ” መፅሄት አምደኛ በመሆን የሰራ ሲሆን በኢቢኤስ ቴሌቪዥን “የብራና ልጆች” የተሰኘ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢም ነበር፡፡