Monday, 05 January 2015 07:53

“ለ6 ወር ያስተማርኩበት ደሞዝ አልተከፈለኝም”

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(110 votes)

መብቴን ለማስከበር ወደ ፍ/ቤት ላመራ እችላለሁ ብለዋል
የፕሮፌሰርነት ማዕረግ አላግባብ መከልከላቸውን ተናግረዋል

 ባለፈው ሳምንት በማህበራዊ ድረ-ገጽ በተሰራጨ መረጃ፣የፖለቲካል ሣይንስ መምህርና የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጡረታ እንደተባረሩ ቢነገርም መረጃው እውነት አለመሆኑን ከአንደበታቸው ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ሆኖም ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈጠረ ችግር እንዳለ ይናገራሉ - ዶ/ር መረራ፡፡ ችግሩ ምን ይሆን? ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፤ይሄንንና ሌሎች ከመምህርነት ሙያቸው ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ጠይቋቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲው ጋር የተፈጠረው ችግር መነሻው ምንድን ነው?
ሁሉንም ሲያልቅ መናገር ይሻላል፡፡ ነገር ግን ለ6 ወር ያስተማርኩበት ደሞዝ አልተከፈለኝም፤ መነሻው ይሄ ነው፡፡ ፓርላማ በቆየሁባቸው ጊዜያትም ደሞዝ አይከፈለኝም ነበር፤ የዩኒቨርስቲው ይበቃሃል ተብዬ፡፡ እዚህም እንግዲህ ለ6 ወር በነፃ እያገለገልኩ ነበር ማለት ነው፡፡
ምክንያቱ ተነግርዎታል ? እርስዎስ አልጠየቁም ?
የቅርብ አለቆች እየተነጋገሩበት ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰጠኝ፡፡ ግን ማስተማሬን አላቆምኩም፤ በነፃ እያገለገልኩ ነው ማለት ነው፡፡ ምናልባት መፍትሄ ካልተገኘ መብቴን ለማስከበር ወደ ፍ/ቤት ላመራ እችላለሁ፡፡   
በዩኒቨርሲቲው ምን ያህል ጊዜ አስተማሩ?
እሱ የአደባባይ ሚስጥር ነው፤ ለ28 አመት ፖለቲካል ሣይንስ አስተምሬያለሁ፡፡
በዩኒቨርስቲው በሃላፊነት የመስራት እድል አጋጥሞት ያውቃል?
አዎ! በሦስት የተለያዩ ጊዜያት የፖለቲካል ሣይንስ ትምህርት ክፍል ተጠሪ ነበርኩ፡፡ ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ በትክክል ባላስታውስም ለመጨረሻ ጊዜ በኃላፊነት የሠራሁት ከሦስት ዓመት በፊት ነው፡፡ ኢህአዴግ ከገባ በኋላ ሦስት ጊዜ ሃላፊ ሆኜ ሰርቻለሁ፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ከመሆንዎ ጋር በተገናኘ በማስተማር ስራዎ ላይ ተጽእኖ ወይም ለየት ያለ ችግር ደርሶብዎት  ያውቃል?
አሁን የተፈጠረው ችግር ሳይፈታ ወደዚህ ጉዳይ ብዙም መግባት አልፈልግም፡፡ ነገር ግን ለሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ካመለከትኩ 6 አመት ቢሆነኝም የረባ ምክንያት ሳይኖር እስካሁን ድረስ አልተሠጠኝም፡፡
 የሌሎቹ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ነው የሚያልቀው፡፡ የእኔ ግን 6 አመት ሆኖታል፡፡ ከዚህ አንጻር አስተዳደራዊ ተፅዕኖ እንዳለ መጠርጠር ይቻላል፡፡ የአሁኑ ችግር እልባት ሲያገኝ ሁሉንም በዝርዝር ልናገር እችል ይሆናል፡፡ ከዩኒቨርሲቲው በጡረታ እንደተባረሩ መረጃዎች ሲናፈሱ ነበር፡፡ ምናልባት የደሞዙ አለመከፈል ከዚሁ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል?
ጡረታ ከተባለ በአፄ ሃይለሥላሴ ዘመን ያስተማሩኝ ሰዎች አሁንም ከኔ ጋር እያስተማሩ ነው፡፡ የ80 አመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑ የውጭ ሀገር ዜጐችም እያስተማሩ ነው፤ ህንዶችን ጨምሮ፡፡ የእኔ ከጡረታ ጋር የተያያዘ ይሆናል ተብሎ እንዴት እንደተገመተም አላውቅም፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውጪ በትርፍ ጊዜዎ በባህር ማዶ ዩኒቨርሲቲዎች ያስተምራሉ ይባላል፡፡ ይህ ምን ያህል እውነት ነው?
አይ እኔ በውጭ ዩኒቨርስቲዎች ተማርኩ እንጂ አላስተማርኩም፡፡ አስተምሬም አላውቅም፡፡ ከሌክቸር ባለፈ በአስተማሪነት ሠርቼ አላውቅም፡፡
ምናልባት ዩኒቨርስቲው ባይፈልግዎት የሚወስዱት አማራጭ ምንድን ነው? በሌላ ዩኒቨርሲቲ የማስተማር ሃሳብ አለዎት?
እኔ አሁን እሱን እያሰብኩ አይደለም፡፡ ግን ከሀገር ውጪ ሄጄ ካላስተማርኩ በቀር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወጥቼ የት እሄዳለሁ? በመላው አገሪቱ ያሉት በአንድ መንግስት ስር የሚተዳደሩ ዩኒቨርሲቲዎች ነው፡፡
40 ያህል የዩኒቨርሲቲ መምህራን ሲባረሩ የቀራችሁት እርስዎና ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ነበራችሁ፤ እንዴት  ከመባረር አመለጣችሁ?
አሁን እንዴት እንደተረፍን አላስታውስም፡፡ እንደውም በወቅቱ አንድ ጓደኛዬ፤ “እንዴት አንተ ቀርተህ እኔ ተባረርኩ” ብሎኝ ነበር፡፡ በዚህ ጉዳይ እንኳ ብዙ የምለው ነገር አይኖረኝም፡፡
በመምህርነት ህይወትዎ ለዩኒቨርሲቲውም ሆነ ለሀገር አበርክቻለሁ የሚሉት ትልቅ ነገር ምንድነው?
ሰው ስለራሱ ባይናገር ይመረጣል፡፡ የሆኖ ሆኖ ሁለት መጽሐፍት አሳትሜአለሁ፡፡ በተደጋጋሚ በሀገር ውስጥና  በውጪ አገር ሌክቸሮችና አለማቀፍ ስብሰባዎች ላይ ተካፍዬ ሃሳቤን ገልጫለሁ፡፡
ፖለቲካንና ሀገሪቷን በሚመለከት ጉዳይ በአለም ታላላቅ በሆኑት እነ ቢቢሲ፣ አልጀዚራ፣ ሲኤንኤን፣ ቪኦኤ እና በመሳሰሉት ላይ አስተያየቶችና ቃለምልልሶችን በስፋት ስሰጥ ነበር፡፡ በአሜሪካና አውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎችም ሌክቸር የማድረጉ አጋጣሚ ነበረኝ፡፡ አካዳሚውንም ፖለቲካውንም በሚዛናዊነት ለማስኬድ ሞክሬያለሁ፡፡
ሁለቱ መፅሐፎችዎ በምን ላይ ያተኮሩ ናቸው?
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ አለማቀፍ ተቀባይነት ባላቸው ጆርናሎች ላይም የተለያዩ ጽሑፎቼ ቀርበዋል፡፡ በአሜሪካ፣ አውሮፓ፣ በአፍሪካና በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ሙሉ የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያላቸው ሰዎች፤ ፕሮፌሰርነት ይሰጠው ብለው ጠንካራ የምስክርነት ድጋፍ (ሪኮመንዴሽን) ከሰጡኝ 5 አመት አልፏቸዋል፡፡ በእኩያ መምህራን ወዳጆቼም፣ በአለቆቼም ሆነ በተማሪዎቼ ግምገማ ከፍተኛ ውጤት አላቸው ከሚባሉት መምህራን አንዱ ነኝ፡፡ ይሄንን ዩኒቨርስቲውም ያውቃል፡፡ ለፕሮፌሰርነት ሳመልክት ከ120 ከተያዘ ውጤት 117.5 ነው ያገኘሁት፡፡ ይሄ ደግሞ እጅግ በጣም ከፍተኛ ከሚባሉት ውጤቶች አንዱ ነበር፡፡
የፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተከለከሉበትን ምክንያት ጠይቀዋል?
ያለፉትም የአሁንም ፕሬዚዳንቶች በሚገባ ጉዳዬንና ጥያቄዬን ያውቃሉ፡፡ ወደታች ያሉትም ያውቃሉ፤ ምንም የተደበቀ ነገር የለውም፡፡ በተደጋጋሚም አስታውሳለሁ፤ ግን ምላሽ የለም፡

Read 13957 times