Saturday, 20 December 2014 12:05

የገና ኤክስፖ ዛሬ ይከፈታል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

የዘንድሮን የገና የንግድ ትርኢትና ባዛር ለማዘጋጀት ጨረታውን በ6.1 ሚሊዮን ብር ያሸነፈው ላቪስን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ፤ የገናን ኤክስፖ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት እንደሚከፍት አስታወቀ፡፡ የገና ኤክስፖ እስከ ታህሳስ 28 የሚቆይ ሲሆን ከ400 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች እንደሚሳተፉበት ታውቋል፡፡ ላቪስን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ፤ በኤክስፖው ለሚሳተፉ፣ ለሚጎበኙና የተለያየ ተሰጥኦ ላላቸው ሽልማቶችን ያዘጋጀ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ በሰባት ታዋቂ ባንዶችና ከመቶ በላይ በሆኑ ታዋቂ ድምፃውያንና ኮሜዲያን ታዳሚውን እያዝናና እስከመዝጊያው እንደሚዘልቅ አስታውቋል፡፡   

Read 1371 times