Saturday, 13 December 2014 11:22

የብዙነሽ በቀለ ዘፈኖች እንደገና ተሰርተው ቀረቡ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(8 votes)

     በበርካታ የድምፃዊ ብዙነሽ በቀለ አድናቂዎች እጅ የማይገኙ 14 ዘፈኖችን ያካተተ “ቃል ኪዳን ተረስቶ” የተሰኘ የሙዚቃ ሲዲ ለአድማጭ ቀረበ፡፡ የእውቋንና ተወዳጇን ድምፃዊት ብዙነሽ በቀለ ዘፈኖች እንደገና የሰራችው “ፍቅሬን ያያችሁ” በሚል ዘፈኗ የምትታወቀው ድምፃዊት ኤልሳቤት ተሾመ እንደሆነች ታውቋል፡፡
የሙዚቃ ሲዲውን ያዘጋጀው “ኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽን” ሲሆን “ፒያሳ ዘ አራዳ ኢንተርቴይንመት” አሳትሞ እያከፋፈለው እንደሆነም ተገልጿል፡፡
 ድምፃዊት ኤልሳቤት ተሾመ፤ ለብዙነሽ በቀለ ቤተሰቦች አስፈላጊውን ክፍያ ከፍላና ስምምነት ፈፅማ እንደሰራችው አዘጋጁ ጠቁሞ፣ ሲዲው ከችግር የፀዳ መሆኑን አስታውቋል፡፡ በሲዲው ላይ “ፍላጎቴ”፣ “ምን ነበር”፣ “ምን በደልኩት ምነው”፣ “ምኞቴን ማን ያውቃል”፣ “አይወጣኝም ክፉ ነገር”፣ “ስምክን ሳላነሳው”፣ “ስንቱን አየሁ ባንተ” እንዲሁም የአልበሙ መጠሪያ የሆነው “ቃል ኪዳን ተረስቶ” እና ሌሎች የብዙነሽ ተወዳጅ ዘፈኖች የተካተቱ ሲሆን ሰሞኑን ገበያ ላይ ውሏል፡፡

Read 5075 times