የአሜሪካ ዲሞክራሲና የአሜሪካ ኢኮኖሚ ስኬታማ የነበሩት በግለሰባዊነት ወይም በማህበረሰባዊነት ብቻ አይደለም፤ በሁለቱም የሚቃረኑ አዝማሚያዎች መስተጋብር ጭምር እንጂ፡፡
ፍራንሲስ ፉኩያማ
(አሜሪካዊ ኢኮኖሚስትና የታሪክ ምሁር)
***
ኮሙኒዝም የሚለውን ስም የሚመጥን አገር ውስጥ ነፃነት የለም፡፡ ህዝቡ ሥልጣንን መጠቀም ይፈልጋል፡፡ ግን ቢሰጠው ምን ይሰራበታል?
ቭላድሚር ኢሊች ሌኒን
(ሩሲያዊ አብዮታዊ መሪ)
***
“ኤሌክትሮኒክ ዲሞክራሲ” ለተሳትፎ አዲስ በር ሊከፍት ይችላል፡፡ ነገር ግን ለሁሉም ችግር መፍትሄ አይሆንም፡፡ ዲሞክራሲ ያለ ዲሞክራሲያዊ ሂደት የቃላት ጋጋታ ብቻ ነው፡፡
ዳግላስ ሹለር
(አሜሪካዊ ደራሲ)
***
በኮምፒዩተር የታገዘ የመረጃ አገልግሎት በዲሞክራሲያዊ ህብረተሰብ ውስጥ ትክክለኛ ቦታ አለው ከተባለ የህዝብ ቤተመፃህፍት ውስጥ ነው፡፡
ቴዎዶር ሮስዛክ
(አሜሪካዊ ፀሃፊና አርታኢ)
***
በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚመራ መንግስት እስካለን ድረስ ውለታ እንዲደረግላቸው የሚፈልጉ ሰዎች አይጠፉም፡፡
ሐሪሰን ደብሊው. ፎክስ ጄአር
(አሜሪካዊ ደራሲ)