“ኢትዮጵያን በጐንደር ብሔራዊ ካርኒቫል” በሚል ርእስ በሚቀርበው ዝግጅት የከተማዋ አስተዳደርየጐብኚዎችንቆይታ በማራዘም የኢትዮጵያን ጥሩ ገፅታ ለማስተዋወቅና የቱሪዝም ፍሰቱን ለመጨመር ያቀደ ሲሆን ዓመቱን ሙሉ ቅስቀሳ መደረጉንም አስታውቋል፡፡ 150ሺ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ጐብኚዎች ከከተማው ነዋሪ ጋር ይታደሙበታል ተብሎ የሚጠበቀውዝግጅት፤ በታሪካዊ ቅርሶችና ትውፊቶች ታጅቦ ይቀርባል ተብሏል፡፡ ዝግጅቶቹ መሃል በኦርቶዶክሳዊ ሥርዓት በወጣቶች የሚቀርብ የቅኔ፣ የአቋቋምና ዜማ፣ የፈረስ ጉግሥና ሠረገላ ትርዒት፣ ነጋሪት ጉሰማ እና እምቢልታ መንፋት፤ በፋሲል ግንብ ውስጥ የባህላዊ ዘፈን ትርዒት እንዲሁም በዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ጊዜ ተካሂዶ የነበረውን የቁንጅና ውድድር የሚዘክር ታሪካዊ ተውኔትና የቁንጅና ውድድር፤ ይገኙበታል፡፡