ለፊልም ባለሙያ ብርሃኑ ሽብሩ ሥራዎች አክብሮት የሚገለፅበት የሥነ ጥበብና ሥነ ራዕይ አውደርእይ ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ረፋዱ ላይ አምስት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዘክር አዳራሽ ተከፈተ፡፡ አርቲስት እመቤት በለጠ እና ዳይሬክተር ብርሃኑ ሽብሩ ያቀረቡት አውደርእይ እስከ ጥር 6 ቀን 2004 ዓ.ም በየቀኑ ከጧቱ 4 ሰዓት እስከ 11 ሰዓት ለሕዝብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ዝግጅቱ የብርሃኑ አድናቂ የሆነችው አርቲስት እመቤት ከኢትዮጵያ፣ ከካናዳ እና ቻይና ልምዷ በመነሳት ያዘጋጀቻቸው ሥዕሎችና የዳይሬክተሩን የሥነ ራእይ ሥራዎች ያካተተ ነው፡ በዚሁ ዝግጅት ኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነፅሁፍ፣ ሥነ ሥዕል እና ፊልም ዙርያ ውይይቶችም እንደሚካሄዱ ተገልጿል፡፡