Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Friday, 06 January 2012 09:33

የሉሲ አካዳሚ ተማሪዎች ገናን በመፃህፍት ስጦታ አከበሩ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጉርድ ሾላ አካባቢ የሚገኘው የሉሲ አካዳሚ ተማሪዎች ገናን (የልደት በዐልን) አርብ እለት በመፃህፍት ስጦታ አከበሩ፡፡ በእለቱ በተከናወነ የመፃህፍት ንባብና የግጥም ውድድር ላሸነፉና በትምህርታቸው ብልጫ ላስመዘገቡ ተማሪዎች ለገና ሥጦታ የተረት መፃህፍት ተበርክተውላቸዋል፡፡ ከጀርመን የባህል ተቋም ጋር በመተባበር በቀረበው ዝግጅት ከ5-12 ዓመት ያሉ ህፃናት ታድመውታል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የመማርያ ቁሳቁስ እና ልብሶች ለሜሪ ጆይ በእርዳታ ሰጥተዋል፡፡ ረቡዕ ጧት በትምህርት ቤቱ ቅፅር ግቢ በተከናወነ ሥነ ሥርዓት የሜሪጆይ ሥራ አስኪያጅ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ከአርቲስት አብራር አብዶ እና አርቲስት ትዕግስት ግርማ ጋር በመሆን እርዳታውን ተረክበዋል፡፡

 

 

Read 2596 times Last modified on Friday, 06 January 2012 09:35