ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር አባል የሆኑት አቶ አረጋዊ ደጀኔ የፃፉት “መገንጠያ” የግጥም መፅሐፍ ነገ ይመረቃል፡፡ “መገንጠያ” የሚመረቀው በሐገር ፍቅር ትያትር ቤት ከጧቱ አራት ሰዓት ነው፡፡በሌላም በኩል “ግጥምን በጃዝ” ኪነጥበባዊ ዝግጅት በመጪው ረቡዕ ከምሽቱ 12 ሰዓት በዋቢሸበሌ ሆቴል ይቀርባል፡፡ 50 ብር የመግቢያ ዋጋ በሚጠየቅበት ዝግጅት የአብርሃም ወልደገብርኤል ግጥም በፉጨት ታጅቦ የሚቀርብ ሲሆን ከዚህም ሌላ አርቲስት ታምሩ ብርሃኑ አጭር ድራማ፤ አርቲስት ግሩም ዘነበ መነባንብ እንዲሁም ሜሮን ጌትነት፣ ኤፍሬም ስዩም፣ ምሥራቅ ተረፈ፣ እና ሌሎችም የግጥም ሥራዎቻቸውን ያቀርቡበታል፡፡