ዕይታ ከበቃ አንድ ወር ያለፈው የቶም ክሩዝ “ሚሽን አምፖሲብል “ዘ ጐስት ፕሮቶኮል” ፊልም በ38.3 ሚሊዬን ዶላር ሳምንታዊ ገቢ የቦክስ ኦፊስን ደረጃ እየመራ እንደሆነ “ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር” አስታወቀ፡፡ በፈረንጆች አዲስ ዓመት የመጀመሪያ ሳምንት አዲስ ፊልም ለገበያ አለመብቃቱን የጠቆመው ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር፤ የቶም ክሩዝ ፊልም ለዕይታ ከበቃ ከወር በኋላ በመላው ዓለም በአጠቃላይ 366.5 ሚሊዮን ዶላር ከ31 በላይ ፊልሞች ላይ የተወነው የ49 ዓመቱ ቶም ክሩዝ፤ እስካሁን 6.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡