Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Friday, 06 January 2012 08:44

ጆርጅ ኩልኒ ኦስካር ሊሸለም ይችላል ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

“ዘ ዲሴንዳንትስ” እና “ዘ አይድያስ ኦፍ ማርች” በተባሉት ፊልሞቹ በፕሮዲውሰር ጊልድ ኦፍ አሜሪካ አዋርድ ለሁለት ሽልማቶች የታጨው ጆርጅ ኩልኒ፤ በተለያዩ የሽልማት ዝግጅቶች ተጋባዥ እየሆነ ከፍተኛ ትኩረት ማግኘቱን ዘ ሎስ አንጀለስ ታይምስ ዘገበ፡፡ የ51 ዓመቱ ጆርጅ ኩልኒ ከ15 ቀናት በኋላ በሚደረገው የ”ፕሮዲውሰር ጊልድ ኦፍ አሜሪካ አዋርድ ላይ በምርጥተዋናይነትና በምርጥ ፕሮዱዩሰርነት የሽልማት ዘርፎች ሊሸለም እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ለጆርጅ ኩልኒ ከፍተኛ ትኩረት ያስገኙለት ሁለቱ ፊልሞች ከ81 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያስገኙ ሲሆን ለዘንድሮው የኦስካር የምርጥ ተዋናይ ሽልማት በመታጨት ያሸንፋሉ ተብለው ከሚጠበቁት ተርታ ተጠቃሽ ሆኗል፡፡

“ዘ ዲሴንዳንትስ” የቤተሰብ ድራማ ሲሆን “ዘ አይድያስ ኦፍ ማርች” የፖለቲካ ጭብጥ ያለው ፊልም ነው፡፡ ላለፉት ሦስት ዓመታት የተባበሩት መንግስታት የሰላም መልዕክተኛ ሆኖ እያገለገለ የሚገኘውና በተለይም በሱዳን ዳርፉር ግጭት ባደረገው የሰላም ጥረት የተመሰገነው ኩልኒ፤ በ”ፒፕል መጋዚን” ለሁለት ዓመታት “የዓመቱ አማላይ ወንድ” ተብሎ የተመረጠ ብቸኛው የሆሊውድ ተዋናይ ሲሆን በ”ታይም” መፅሄት ከዓመቱ ተፅእኖ ፈጣሪ 100 ታዋቂ ግለሰቦች ተርታ ለአራት አመታት በመመረጥ ከፍተኛ ክብር ተቀዳጅቷል፡፡ ከቴሌቪዥን ፊልሞች ተዋናይነት በመነሳት በትላልቅ ፊልሞች ላይ የተወነው ጆርጅ ኩልኒ ከ29 በላይ ፊልሞች ላይ ተውኗል፡፡

 

 

 

Read 2090 times Last modified on Friday, 06 January 2012 08:47