Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Friday, 06 January 2012 08:43

50 ሴንት ተስፋ ቆርጧል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ያለፉትን ሁለት ዓመታት በፊልም ስራ ፕሮጀክቶቹ ተጠምዶ የቆየው ራፐሩ 50 ሴንት፤ ረዥም ዕድሜ የለኝም በሚል ስሜት ተስፋ መቁረጡን ከሮሊንግ ስቶን መፅሄት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ገለፀ፡፡ ራፕሩ ራሴን የማጠፋ ሰው አይደለሁም፤ ህይወቴ ግን አጭር ሆኖ ይሰማኛል፤ የሙዚቃ ስራዬም ሰልችቶኛል” ሲል ተናግሯል፡፡ ራፐሩ ከጥቂት ሳምንት በፊት “50 ሴንት ኢን ዘ ፊውቸር” የተባለውን ነጠላ ዜማ ቢለቅቅም ሌሎች አዲዲስ ዘፈኖቹን ያካተተውን “ዘ ብላክ ማጂክ” የተሰኘውን አምስተኛ አልበሙን በቅርቡ ለገበያ እንደማያበቃ  ገልጿል፡፡ አልበሙን ከሚሰራለት ኩባንያ ጋር ያለፉትን ወራት በውዝግብ መቆየቱን የጠቆመው ኤምቲቪ ኒውስ፤ ለአልበሙ 41 ዘፈኖችንመቅረፁንአስታውቆወደገበያውስለመግባቱማረጋገጫአልተገኘም ብሏል፡፡ የሃብት መጠኑ እስከ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚገመተው 50 ሴንት፤ ለኮካኮላ እና ለቪታሚን ውሃ ለሚሰራቸው ማስታወቂያዎች በሚሊዮን ዶላሮች የሚገመት ውል ተፈራርሟል፡፡

 

 

Read 2925 times Last modified on Friday, 06 January 2012 08:47