Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Friday, 06 January 2012 08:36

አሬታ ፍራንክሊን ህይወቷን በትዳር ማጣፈጥ ትፈልጋለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የ69 ዓመቷ የሙዚቃ ባለሙያ አሬታ ፍራንክሊን ከረጅም ጊዜ ወዳጇ ከዊል ዊልከሰርን ጋር ቀለበት እንዳሰረች ተገለፀ፡፡ በቅርቡ “አሬታ፡ኤውመንፎሊንግ አውት  ኦፍ ላቭ” የተባለ አዲስ አልበም ለገበያ ያበቃችው አቀንቃኟ፤ ከአሁኑ እጮኛዋ በፊት ሁለትጊዜ አግብታ ፈታለች፡፡ ባለፈውዓመትከሰውነት ክብደቷ 85 ፓውንድ በመቀነስ ሸንቀጥቀጥ ያለችው አሬታ ፍራንክሊን፤ ወጣትነት ይሰማኛል በማለት መናገሯን ያስታወሰው ዘ ፒፕል መፅሄት፤የመጨረሻ እድሜዋን በትዳር ጣፋጭ የማድረግ ፍላጐት እንዳላት መናገሯን ጠቅሷል፡፡ አሬታና እጮኛዋ ዊሊ  ከስድስት ወራት በኋላ የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን በደመቀ ሁኔታ በሚያሚ ፍሎሪዳ ውስጥ ውድ የመዝናኛ መርከብ በመከራየት ለመፈፀም ማቀዳቸውም ተዘግቧል፡፡ አሬታ የሙሽራ ልብሷን ለማርያ ኬሪ፤ ለኡማ ቱርማንና ለሻሮን ስቶን አስደናቂ ዲዛይኖች በሰራችው ቬራ ዋንግ ለማሰራት መወሰኗንም መፅሄቱ ጠቁሟል፡፡ የሶል ሙዚቃ ንግስት የምትባለው አሬታ ፍራንክሊን 18 ግራሚ ሽልማቶችን የወሰደች አንጋፋ ሙዚቀኛ ናት፡፡

 

 

Read 2688 times Last modified on Friday, 06 January 2012 08:41

Latest from