Saturday, 25 October 2014 10:35

የፍቅር ጥግ

Written by 
Rate this item
(5 votes)

(ስለአማች)
አዎ፤ ህይወት የተሻለ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የከፋም ሊሆን ይችላል፡፡ አላመንሽኚም? እንግዲያውስ ከአማችሽ ጋር እንዳስተዋውቅሽ ፍቀጂልኝ፡፡
ጃሮድ ኪንትዝ
አማቴ በጣም ተናደውብኝ ሁለተኛ እንደማያናግሩኝ ምለው ተገዘቱ፡፡ እኔም ፈገግ አልኩና ፈጣሪ ላደረገልኝ ትንሽዬ ተዓምር ምስጋናዬን አቀረብኩ፡፡
ጃሮድ ኪንትዝ
ከአማቴ ጋር ምንም ዓይነት በጎ ግንኙነት ባይኖረንም “እማዬ” ብዬ እንድጠራቸው መወትወታቸውን አልተዉም፡፡
ጄምስ ሳንድሮ
የምታገባትን ሚስት በምናብህ ስትስል አማትህንም እንዳትዘነጋ፡፡
ያልታወቀ ሰው
ከእያንዳንዱ የተሳካለት ወንድ ጀርባ ተጠራጣሪ አማት ቆመዋል፡፡
ያልታወቀ ሰው
በማለዳ ጸዳልና በአማትሽ ፈገግታ እርግጠኛ አትሁኚ፡፡
የጃፓኖች አባባል
አዳም በዓለም ላይ ዕድለኛው ሰው ነበር - አማት አልነበረውም፡፡
ሾሎም አሊቼም
 ከአስደሳች ጉዞ መመለሴ ነው፡፡ አማቴን ኤርፖርት አድርሼ መጣሁ፡፡
ሔኒ ያንግማን
አማቴን ለሁለት ዓመት ያህል አላነጋገርኳቸውም፡፡ ከዝምታቸው ላናጥባቸው አልፈለግሁም፡፡
ኬን ዶድ -
ከእያንዳንዱ ስኬት ጀርባ የኮራች ሚስትና ተጠራጣሪ አማት አሉ፡፡
ብሩክ ሃይስ

Read 2076 times