Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 31 December 2011 12:16

ሰሎሞን ቦጋለ ”የበዓል እንግዶች” ላይ ሊተውን ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

ከመጪው የካቲት ወር አጋማሽ ጀምሮ ሀገር ፍቅር ትያትር ቤት ዘወትር እሁድ መታየት በሚጀምረው “የበዓል እንግዶች” የተሰኘ አዲስ ቴአትር ላይ ሰሎሞን ቦጋለ እንደሚተውን ተገለፀ፡፡ በዘካርያስ ብርሃኑ ተፅፎ በዘውዱ አበጋዝ በሚዘጋጀው “የበዓል እንግዶች” ሳታየር ኮሜዲ ላይ በተጋባዥ እንግድነት የሚተውነው ሰሎሞን ቦጋለ፤ በቅርቡ በፊልም “ምርጥ የወንድ ተዋናይ” ተብሎ መሸለሙ ይታወሳል፡፡ ከፊልም በፊት ትያትር የጀመረው አርቲስት ሰለሞን፤ በ16 ትያትሮች ላይ የተወነ ሲሆን በ43 ፊልሞች ላይ በመሪ ተዋናይነት ተሳትፏል፡፡ በትያትር ቤቱ ግብዣ የሚተውነው ሰለሞን ቦጋለ፤ ሀገር ፍቅር ትያትር ቤት በተዋናይነት ተጋብዞ ሲሳተፍ የመጀመርያው ነው፡፡ ከሱ ሌላ ትዕግስት ግርማ፣ ሸዊት ከበደ፣ ተስፋ ብርሃኔ፣ ሃና ተፈረ እና ታደለ በትያትሩ ላይ ይተውናሉ፡፡ ሰለሞን ቦጋለ ከሚተውንባቸው ፊልሞች መካከል “ቤተልሔም” እና “የትሮይ ፈረስ” አሁን እየታዩ ያሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘወትር ረቡዕ ምሽት እየታየ ባለው “ሰው ለሰው” ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ላይ መርማሪ ፖሊስ ሆኖ እየተወነ ይገኛል፡፡

 

 

Read 2892 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 12:36

Latest from