Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 11:59

የጐልደን ግሎብ እጩዎች ታወቁ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ዘንድሮ ለሚካሄደው ለ69ኛው የጐልደን ግሎብ ሽልማት የተመረጡ እጩዎች ሰሞኑን ይፋ የተደረጉ ሲሆን ለ84ኛ የኦስካር አዋርድ እጩዎችን ለመምረጥ ድምጽ የመስጠት ስነስርዓት መጀመሩ ተገለፀ፡፡ከሦስት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው 69ኛው የጎልደን ግሎብ ሽልማት የሚፎካከሩ ዕጩዎች ሰሞኑን የታወቁ ሲሆን “ዘ አርቲስት” የተሰኘው ፊልም ለ6 የሽልማት ዘርፎች በመታጨት እንደሚመራ ታውቋል፡፡ በወንዶች የ”ምርጥ ተዋናይ”  ሽልማት ዘርፍ:- ጆርጅ ኩልኒና ሊዮናርዶ ዲካርፒዮ እንዲሁም በሴቶች:- ኬት ዊንስሌት “ሚልድሬድ ፒርስ” በተባለ የቲቪ ሾውና “ካርናጌ” በተባለው ፊልም ላይ ባሳየችው ድንቅ ትወና በእጩነት ተመርጠዋል፡፡ በምርጥ ዲያሬክተርነት  ከታጩት መካከል ደግሞ ማርቲን ስኮርሴሲ እና ውዲ አለን ይጠቀሳሉ፡፡

 

 

 

Read 2432 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 12:05