Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 31 December 2011 11:56

በአዲሱ የፈረንጆች ዓመት የሆሊዉድ ፊልሞች ገበያ እንደሚደራ ተገለፀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በተጠናቀቀው የ2011 የፈረንጆች አመት የሆሊውድ ፊልሞች ገቢ ከዓምናው በ1 ቢሊዮን ዶላር የቀነሰ ቢሆንም በ2012 ለእይታ ይበቃሉ ተብለው በሚጠበቁ በርካታ ፊልሞች የሆሊውድ ገበያ እንደሚደራ ተገለፀ፡፡ በአዲሱ የፈረንጆች አመት 27 የምርጥ ፊልሞች ተከታይ ክፍሎች፤11 ምርጥ የአኒሜሽን ፊልሞች፤ ከ29 በላይ የኮሜዲ ፊልሞች በ3ዲ ቴክኖሎጂ  በድጋሚ ለእይታ እንደሚበቁ “ዘ ሆሊውድ ሪፖርተር” ጠቁሟል፡፡ “ዘ ዳርክ ናይት ራይዝስ”፤ “ዘ አሜዚንግ ስፓይደርማን”፤ “ዘ አቬንጀርስ” እና ሁለቱ የአኒሜሽን ፊልሞች “አይስ ኤጅ” እና “ማዳጋስካር” በአዲሱ ዓመት ለዕይታ ከሚወጡ ፊልሞች ተጠቃሽ ሲሆኑ “ፋይንዲንግ ኔሞ”፤ “ቢውቲ ኤንድ ዘ ቢስት” እና ”ስታር ዋርስ” በ3ዲ ለእይታ ይበቃሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በ2011 የሆሊዉድ ፊልሞች ገቢ ከተመልካች ማነስ ጋር በተያያዘ መቀዛቀዙን የጠቆመው ቦክስ ኦፊስ ሞጆ እንዲህ ያለ የገቢ መቀዝቀዝ ከ16 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተመዘገበ አመልክቷል፡፡

 

 

Read 2801 times Last modified on Saturday, 31 December 2011 11:59

Latest from