Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 31 December 2011 11:52

“አዲስ ጉዳይ” መፅሔት 5ኛ ዓመቷን አከበረች

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ቀድሞ “ሮዝ” ትባል የነበረችው “አዲስ ጉዳይ” ባለቀለም መፅሔት የተመሰረተችበትን አምስተኛ ዓመት ባለፈው ቅዳሜ ምሽት በሒልተን አከበረች፡፡ የአከባበር ሥነ ሥርዓቱ በቅርቡ በድንገት ሕይወቷ ያለፈውን የመፅሔቷ ምክትል ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ፅጌረዳ ሃይሉ በሕሊና ፀሎት በማሰብ የተጀመረ ሲሆን መፅሔቷን የተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍም ቀርቧል፡፡ በአከባበሩ ላይ ታዋቂ ግለሰቦች ንግግር ያደረጉ ሲሆን ከነዚሁ መካከል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እና በመድረክ ወግ አቅራቢነቱ የሚታወቀው የስታትስቲክስ ባለሙያ በኃይሉ ገብረመድህን መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡በወር ሁለት ጊዜ ለንባብ የምትበቃውን መፅሔት ሳምንታዊ ለማድረግም እቅድ መያዙን ማወቅ ተችሏል፡፡

Read 3403 times