በደራሲ ወንድሙ ነጋሽ የተፃፈው “የአዕምሮ ጉዳይ” የተሰኘ መፅሃፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ አዕምሯችን የማናውቀው ፕላኔት ነው የሚለው መፅሃፉ፤ ስለ አእምሮ ህመምና ማህበረሰቡ ለአእምሮ ህመምተኞች ስላለው አመለካከት፣ ለአዕምሮ መታወክ መንስኤ ስለሚሆኑ ጉዳዮችና መፍትሄዎቻቸው… የሚዳሰስስ ነው፡፡ በ192 ገፆች የተቀነበበው መፅሀፉ፤ በ39 ብር ከ60 ለገበያ የቀረበ ሲሆን የመፅሀፉ ሽያጭ ገቢ በአዕምሮ ህመም ለሚሰቃዩ ወገኖች ለሚቋቋመው ድርጅት መርጃ ይሆናል ተብሏል፡፡ ደራሲው ከዚህ ቀደም “የአዕምሮ አስተዳደር ሞዴል” እና “ፍቅር ምንድን ነው” የሚሉ መፃህፍትን ለአንባቢያን ማድረሳቸው ይታወቃል፡፡
Saturday, 16 August 2014 11:06
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና