Saturday, 16 August 2014 10:54

“አገራትን ያናወጡ ሰላዮች” እና “ጊነስ የዓለም ድንቃድንቅ ታሪኮች” ለንባብ በቁ

Written by 
Rate this item
(20 votes)

በተለያዩ የዓለም አገራት ከፍተኛ ነውጥ በፈጠሩ ሰላዮች ላይ ያተኮረው የፈቃዱ ሺፈታ “አገራትን ያናወጡ ሰላዮች” የተሰኘ መፅሀፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ 135 ገፆች ያሉት መፅሀፉ፤ በ40 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡
በየዓመቱ የአለም ድንቃድንቅ ታሪኮችን ከሚያወጣው “ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ” ተመርጠው ወደ አማርኛ የተተረጎሙ አስደናቂ ታሪኮችን የያዘ “ጊነስ የዓለም ድንቃድንቅ ታሪኮች” መፅሀፍ ለአንባቢያን ደረሰ፡፡ በ126 ገፆች የተሰናዳውን መፅሃፍ ተርጎሞ ያቀረበው እስክንድር ስዩም ሲሆን መፅሀፉ በ37 ብር ከ45 ሳንቲም እየተሸጠ ነው፡፡

Read 18352 times