Saturday, 16 August 2014 10:42

ሳሙኤል ይርጋ ተስፋ ከሚጣልባቸው 50 አፍሪካውያን ወጣቶች አንዱ ነው ተባለ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ኢትዮጵያዊው የፒያኖ ተጫዋች ሳሙኤል ይርጋ ታዋቂው “ዘ አፍሪካ ሪፖርት” መጽሄት ሰሞኑን ባወጣው ‘የአመቱ ተስፋ የሚጣልባቸው 50 አፍሪካውያን ወጣቶች’ ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ተገለፀ፡፡
በተለያዩ የሙያ መስኮች ተጠቃሽ ተግባራትን እያከናወኑ የሚገኙ አፍሪካውያን ወጣቶችን በጥናት ላይ ተመስርቶ በመምረጥ በየአመቱ የሚያወጣው መጽሄቱ፣ ዘንድሮም ሳሙኤልን ጨምሮ በንግድ ስራ፣ በፈጠራና በሌሎች የተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ 50 አፍሪካውያን ወጣቶችን ይፋ አድርጓል፡፡
በ16 ዓመት ዕድሜው ወደ ሙዚቃ የገባው ሳሙኤል፣ ለረጅም አመታት በፒያኖ ተጫዋችነት እንደሰራና ‘ጉዞ’ የተሰኘ የመጀመሪያ አልበሙን ለአድማጭ ማቅረቡን የገለጸው መጽሄቱ፣ በኢትዮጵያ የጃዝ ሙዚቃ የራሱን አሻራ በማሳረፍ ላይ ያለ ትልቅ ተስፋ የሚጣልበት ወጣት መሆኑን ዘግቧል፡፡ በዘንድሮው “ዘ አፍሪካ” ሪፖርት መጽሄት ‘የአመቱ ተስፋ የሚጣልባቸው 50 አፍሪካውያን ወጣቶች’ ዝርዝር ውስጥ የኦስካር ተሸላሚዋ ኬንያዊት የፊልም ተዋናይ ሉፒታ ንዮንጎንና ታዋቂውን ናይጀሪያዊ ደራሲ ቺካ ኡኒግዌን የመሳሰሉ አፍሪካውያን ወጣቶች ተካተዋል፡፡

Read 1837 times