Saturday, 16 August 2014 10:28

አቶ ሙሼ ሰሙ ከፓርቲ ፖለቲካ ራሳቸውን አገለሉ

Written by  አበባየሁ ገበያው
Rate this item
(19 votes)

        በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢዴፓ) ለአለፉት 15 ዓመታት በዋና ጸሃፊነት፣ በህዝብ ግንኙነትና በፕሬዚዳትነት ያገለገሉት አቶ ሙሼ ሰሙ፤ ራሳቸውን ከፖለቲካ ፓርቲ ው አገለሉ፡፡
“ራሴን ከፖለቲካ  ያገለልኩት ፋታ በመውሰድ ቆም ብዬ ስለትግሉ ሂደትና ወደፊት ማድረግ ስላለብኝ ነገር ማሰብ ስለምፈልግ ነው” ያሉት አቶ ሙሼ፤ እንደማንኛውም ሰው ስለቤተሰቤ፣ ስለትምህርቴ፣ ስለህይወቴ ማሰብ ያስፈልገኛል” ብለዋል፡፡
በቀጣይ በትርፍ ጊዜያቸው የኢዴፓን አላማና አቋም ለማጠናከር እንደሚሰሩ የተናገሩት አቶ ሙሼ፤ አሁን ያሉት አመራሮች የፓርቲውን የፖለቲካ ስራ በአግባቡ እንደሚወጡ፣ ትግሉንም እንደሚቀጥሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡
 “እንደ ፓርቲ አባልነት ሃላፊነት ወስጄ ባይሆንም በፍላጎት በፖለቲካ ውስጥ የራሴን ሚና እጫወታለሁ” ያሉት አቶ ሙሼ፤ “የፖለቲካ ትግሌም ሆነ ድጋፌ ከሌላ ፓርቲ ጋር ሣይሆን  ከኢዴፓ ጋር የተሳሰረ ይሆናል”  ብለዋል፡፡
ኢዴፓን ለ5 ዓመት በፕሬዚዳንትነት የመሩት አቶ ሙሼ፤ ባለፈው ዓመት ከሃላፊነት የለቀቁ ሲሆን በፓርቲው ውስጥ እስከ ዛሬ የቆዩት ፓርቲው ጊዜና ትንፋሽ ሳያገኝ መልቀቅ ባለመፈለጋቸው እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

Read 4903 times