Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 December 2011 09:13

አይቤክስ ተማሪዎቹን ዛሬ ያስመርቃል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

የቱሪዝም ጋዜጠኞች ፎረም ይቋቋማል

አይቤክስና የሆቴልና ቱሪዝም ኮሌጅ በሆቴል፣ ምግብ ዝግጅት፣ መስተንግዶ፣ በእንግዳ አቀባበል እና በቱሪዝም ማኔጅመንት፣ ጋይድና ኦፕሬሽን ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 320 ተማሪዎች ዛሬ ጧት 2፡30 ያስመርቃል፡፡ ቦሌ በሚገኘው ደሳለኝ ሆቴል የሚመረቁት ተማሪዎች  በግዮን፣ በሐርመኒ፣ በግሎባል እና በሌሎች የአዲስ አበባ ትልልቅ ሆቴሎች የተግባር ልምምድ ያደረጉ ናቸው፡፡ የኮሌጁ ዲን አቶ ገዛኸኝ ብሩ ተማሪዎቹ ከምረቃ በኋላ ሥራ የማግኘት እድላቸውን አስመልክቶ ከአዲስ አድማስ ተጠይቀው፤ የሥራ ገበያ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ስላለ አብዛኞቹ ገና ትምህርት ሳይጨርሱ የቅጥር ቅፅ እንደሚላክላቸውና ሲጨርሱ እንደሚቀጠሩ ተናግረዋል፡፡  በ2001 ዓ.ም በኮሌጅነት ሥራ የጀመረውና በአሁኑ ሰአት 170 ተማሪዎች በአንድ ጊዜ   ተቀብሎ የሚያስተናግደው ኮሌጅ የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ 670 ተማሪዎች (የአጫጭር ጊዜ ሰልጣኞችን ሳያካትት) አስመርቋል፡፡

 

 

Read 2495 times Last modified on Saturday, 24 December 2011 09:17