Saturday, 12 July 2014 11:58

የላሊበላን አብያተ-ክርስቲያናትና የፋሲል ቤተመንግስትን በናኖ ቴክኖሎጂ ለማደስ ታቅዷል

Written by 
Rate this item
(8 votes)

            ጥንታውያኑ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና የጎንደር ፋሲለደስ አብያተ መንግስታት ህንፃዎች ለዘመናት ሳይፈራርሱ እንዲቆዩ ለማድረግ ያስችላል በተባለው ናኖ ቴክኖሎጂ ለማደስ ታቅዷል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን መስፍን፤ ቴክኖሎጂው በዓለም ላይ እየተስፋፋ እንደሆነ ጠቁመው፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲም የናኖ ቴክኖሎጂ ማዕከል አቋቁሞ በቅድሚያ በአብያተ ክርስቲያናቱና ቤተመንግስቱ ህንፃዎች ላይ ቴክኖሎጂውን ቻመተግበር እቅድ መያዙን፤ በቀጣይ ዓመትም ፕሮጀክቱ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡
የፊዚክስ የፈጠራ ውጤት የሆነው ናኖ ቴክኖሎጂ ከሞሎኪዮሎች (ቅንጣቶች) የተፈጠረ ሲሆን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ለህንፃ ግንባታዎችና እድሳቶች ከዋለ፣ ለህንፃው ጥንካሬና እድሜ ይሰጠዋል ተብሏል፡፡
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ናኖ ቴክኖሎጂን በሃገራችን ለማስተዋወቅ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ጠቁመው፤ “ናኖ ግሎባል” ከሚባል ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት መፈረሙን ገልፀዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂው ማዕከል የተቋቋመ ሲሆን የቴክኖሎጂው ሊህቃን ከውጭ ሀገር መጥተው የላሊበላና ጎንደር አብያተ ክርስቲናትና ቤተመንግስታት እንዴት ይቀቡ በሚለው ላይ የምርምር ስራዎችን ያከናውናሉ ብለዋል፤ አቶ ሰለሞን፡፡
ቴክኖሎጂው በምግብ ሳይንስ፣ በኤሌክትሮኒክስ ቁሶች፣ በኢነርጂ፣ በህክምና፣ በህንፃዎች ወዘተ ላይ እየተሰራበት ሲሆን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚከፈተው ማዕከል ለወደፊት አቅሙ ሲጠናከር የመኪና አካላትንም በቴክኖሎጂው ለመቀባት እቅድ መያዙ ተጠቁሟል፡፡

Read 2448 times