Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 24 December 2011 09:05

ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር እና ተጠሪው ተሸለሙ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ጥናትና ምርምን መሠረት በማድረግ በሚያዘጋጃቸው ተከታታይ የሬዲዮ ድራማዎችና  በሚያሳትማቸው መፃሕፍት የሚታወቀው ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር የግሎባል ሚዲያ አዋርድ ተሸላሚ ሆነ፡፡ ሽልማቱ ዋሺንግተን በሚገኘው ፖፕሌሽን ኢንስቲትዩት የተሰጠ ሲሆን ጥር 3,2004 ዓ.ም በኒውዮርክ በሚካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርአት ላይ ለመገኘት የፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር የኢትዮጵያ ተጠሪ ዶክተር ንጉሤ ተፈራ ወደ አሜሪካ ይጓዛሉ፡፡ ፖፕሌሽን ሚዲያ ሴንተር ባለፉት 11 ዓመታት በኢትዮጵያ የጤናና ማህበራዊ ችግሮች ላይ ያተኮሩ እና የባህርይ ለውጥ አምጥተዋል የተባሉ አምስት ተከታታይ የሬዲዮ ድራማዎችን እንዲሁም አስር የአጫጭር ልቦለድ መድበሎችን እና ሌሎች መፃሕፍትን   ያሳተመ ሲሆን ጋዜጠኞችን ጨምሮ ለ1600 የተለያዩ ባለሙያዎች ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ በሌላም በኩል የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ ዶ/ር ንጉሤ ተፈራ የ2011 “የአፍሪካ  ቸርማን አዋርድ ፎር ኤክሰለነስ ኢን ኮሚኒኬሽን ስትራተጂ” ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ ባለፉት አርባ ዓመታት በጋዜጠኝነትና ሚዲያ ኮሙኒኬሽን በተለያዩ የሐላፊነት ደረጃዎች የሰሩት ዶ/ር ንጉሤ፤ በኤች አይቪ ኤድስን መከላከል እና ሥነተዋልዶ ጤናን በማስፋፋት ውጤታማ ሥራ እንደሰሩና የኢትዮጵያ የሥነ ሕዝብ ፖሊሲ ሲቀረፅ በሃላፊነት እንዳስተባበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

Read 3066 times Last modified on Saturday, 24 December 2011 09:08

Latest from