Print this page
Saturday, 05 July 2014 00:00

በአፋር ዲቾ ኦቶ ከተማ በደረሰው የእሳት አደጋ የ30 ሚ.ብር ንብረት ወደመ

Written by  አበባየሁ ገበያው
Rate this item
(3 votes)

ከሰመራ ከተማ በሰባ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ዲቾ ኦቶ ከተማ በደረሰው የእሳት አደጋ 40 ያህል መኖሪያ ቤቶችና ንግድ ቤቶች ሲቃጠሉ፣ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት መውደሙ ተጠቆመ፡፡
ባለፈው እሁድ ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ላይ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ መኖርያ ቤቶች፣ ቡቲኮች፣ ሱቆች፣ ክሊኒክና ሆቴሎች የወደሙ ሲሆን የአደጋው መንስኤ የኤሌክትሪክ ፍንዳታ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የፆም ወቅት በመሆኑና በቃጠሎው ሰዓት የተኛ ሰው ስላልነበረ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ አደጋ የለም እንጂ የከፋ ጉዳት ሊያጋጥም ይችል ነበር ተብሏል፡፡
ለ30 ደቂቃ በቆየው የእሳት ቃጠሎ በጠቅላላው ከ30 ሚ. ብር በላይ ንብረት መውደሙን የጠቆሙት ምንጮች፤ በርካታ ነዋሪዎችም ቤታቸውን አጥተው በየበረንዳውና በየዘመድ ቤቱ ተጠግተው እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡ የዲቾ ኦቶ ከተማ የሙቀት መጠኑ 44 ዲ.ሴ ሲሆን መኖሪያ ቤታቸውን በእሳት ቃጠሎ ያጡት ነዋሪዎች የአደጋና ዝግጁነት ቢሮ ከሚያቀርብላቸው ንፁህ የመጠጥ ውሃ በስተቀር ምን እርዳታ እንዳላገኙ የገለፁት ምንጮች፤ የአደጋው ተጐጂዎች  የመንግስትን አፋጣኝ ምላሽ ይፈልጋሉ ብለዋል፡፡

Read 1936 times