የ30 ዓመቷ ብሪትኒ ስፒርስ ጄሰን ትራዊክ ከተባለ የረጅም ጊዜ ፍቅረኛዋ ጋር ሰሞኑን በላስቬጋስ ቀለበት አሰረች፡፡ በፖፕ የሙዚቃ ስልት ላለፉት 18 ዓመት በመስራት ከፍተኛ ክብርና ዝና የተቀዳጀችው ብሪትኒ፤ መቼ ጋብቻዋን እንደምትፈጽም የታወቀ ነገር የለም፡፡ አዲሱ ዕጮኛዋ ጄሰን ትራዊክ 90ሺ ዶላር የሚያወጣ 3.5 ካራት ዳይመንድ ቀለበት እንዳሠረለት ታውቋል፡፡ በዓለም ዙሪያ 100 ሚሊዮን የአልበሟቿን ቅጂ በመቸብቸብ ስኬታማ የሆነችው ብሪትኒ ስፒርስ፤ የሃብት መጠኗ እስከ 140 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ይገመታል፡፡