Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 December 2011 08:57

ኪም ጆንግ አል የፊልም ወዳጅ ነበሩ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በሳምንቱ መግቢያ ላይ በ69 ዓመታቸው የሞቱት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኒል የፊልሞች ወዳጅ እንደነበሩ ቢቢሲ አስታወቀ፡፡ ኪም ጆንግ ኢል ሲኒማ በኪነጥበብና ስነጽሑፍ ዕድገት ጉልህ ስፍራ እንዳለው በይፋ መናገራቸውን ያወሳው ዘገባ፤ ለአብዮታዊ ርምጃዎችና ለአገር ግንባታ ኃያል መሣሪያ መሆኑን ያመኑ መሪ ነበር ብሏል፡፡ ኪም ጆንግ ኢል የሰሜን ኮርያ መሪ ከመሆናቸው በፊት በበርካታ ፊልሞች የጽሑፍ፣ የዝግጅትና ዲያሬክቲንግ ስራዎች መሳተፋቸውን የሚገልፁ መረጃዎች፤ ተማሪ በነበሩበት ጊዜ የሚያደንቁትን የጃኪ ቻን ፊልሞች ለሰዓታት ደጋግመው ይመለከቱ እንደነበር አመልክተዋል፡፡ መሪ ከሆኑም በኋላ ኪም ጆንግ ኢል በዋና ከተማቸው ሲኦል የሲኒማ ላይብረሪ ያቋቋሙ የሚገለጽ ሲሆን በዚሁ የሲኒማ ላይብረሪያቸው ከ20ሺ በላይ የሆሊዉድ፣ የጃፓንና የሌሎች አገራት ፊልሞችን ማሰባሰባቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

Read 2005 times Last modified on Saturday, 24 December 2011 08:59