የሮይተርስ ዘገባ በመላው ዓለም በሆሊዉድ ፊልሞች የተሰበሰበው ገቢ ከባለፉት ዓመታት በ4በመቶ የወረደ መሆኑንም ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል በ2011 በቻይና ፊልም ሰሪዎች ለአገር ውስጥ ገበያ በቀረቡ 500 ፊልሞች ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የፃፈው “ፒፕልስ ዴይሊ” ጋዜጣ፤ ቻይና በሆሊዉድ ፊልሞች ዓለምአቀፍ ገቢ እስከ 17በመቶ ድርሻ መውሰዷን አውስቷል፡፡ የቻይና ፊልም ሠሪዎች ከሆሊዉድና ከሌሎች ታላላቅ የፊልም ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ጋር በትብብር መስራታቸው ለገቢው መጨመር አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል፡ በተያያዘ “ዘ ሂንዱስተን ታይምስ” የተባለው ጋዜጣ ባሰራጨው መረጃ ዘንድሮ በህንድ ቦሊዉድ በተሠሩ ፊልሞች ዓለም አቀፍ ገቢ በ45 በመቶ ማደጉን ገልጿል፡፡