Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 24 December 2011 08:50

በፊልም ቻይናና ህንድ ገቢያቸው ሲጨምር የሆሊዉድ ቀንሷል

Written by 
Rate this item
(0 votes)

በ2011 የዓለም የፊልም ኢንዱስትሪ ገበያ ላይ በቻይና እና በህንድ የተሠሩ ፊልሞች የአገር ውስጥ ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጨምር የሆሊዉድ ፊልሞች ግን ከ16 ዓመታት ወዲህ ዝቅተኛ የተባለውን ገቢ እንዳስገኙ ሮይተርስ አስታወቀ፡፡ በ2012 አዲስ አመትና የፈረንጆች ገና በዓላት ዋዜማ በሆሊዉድ ለገበያ የበቁ ፊልሞች ገቢ በሰሜን አሜሪካ ብቻ በ12በመቶ መውረዱ ተወስቷል፡፡

የሮይተርስ ዘገባ በመላው ዓለም በሆሊዉድ ፊልሞች የተሰበሰበው ገቢ ከባለፉት ዓመታት በ4በመቶ የወረደ መሆኑንም ገልጿል፡፡ በሌላ በኩል በ2011 በቻይና ፊልም ሰሪዎች  ለአገር ውስጥ ገበያ በቀረቡ 500 ፊልሞች ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የፃፈው “ፒፕልስ ዴይሊ” ጋዜጣ፤ ቻይና በሆሊዉድ ፊልሞች ዓለምአቀፍ ገቢ እስከ 17በመቶ ድርሻ መውሰዷን አውስቷል፡፡ የቻይና ፊልም ሠሪዎች ከሆሊዉድና ከሌሎች ታላላቅ የፊልም ኢንዱስትሪ ኩባንያዎች ጋር በትብብር መስራታቸው ለገቢው መጨመር አስተዋጽኦ ማድረጉ ተገልጿል፡ በተያያዘ “ዘ ሂንዱስተን ታይምስ” የተባለው ጋዜጣ ባሰራጨው መረጃ ዘንድሮ በህንድ ቦሊዉድ በተሠሩ ፊልሞች ዓለም አቀፍ ገቢ በ45 በመቶ ማደጉን ገልጿል፡፡

 

 

 

Read 2999 times Last modified on Saturday, 24 December 2011 08:57