Monday, 19 December 2011 13:59

አሴ በሰባት ዓመትህ - እንካ ራስክን ላጋራህ!

Written by  ነ.መ
Rate this item
(0 votes)

 

ነ.መ
አሴ በሰባት ዓመትህ - እንካ ራስክን ላጋራህ!
አሴ በሰባት ዓመትህ - እንካ ራስክን ላጋራህ!
ዕውነት ለመናገር ግና፣ ሁለት ሰው ይበቃል ይሏል
አንድ አድማጭ፣ አንድ ነጋሪ፤ ጉዳዩን ይጨርሱታል፡፡
ዕውነተኛ ግጥም አሴ፣ ሙቅ ብርድ ልብስህ ነውና
ዋና ፍስሀ ይሆናል፣ ለውስጣችን ግለት ጤና!
አሴ! ይገርምሀል ደግ አጠረ
የቁም ሙት እየወፈረ
ቁመት ወርድ እየጨመረ
ለቀስተኛ እየጨፈረ
የዕውነት ሟች ከርሞ እየከሳ
ስሙም መልኩም ጥቅሙም ሳሳ!
እያደር ይሞላል ያልነው፤ ያፈሳል እንዴ ታሪኩ
ሽንቁር አለው ወይ ትውልዱ፣ ዕውነት የት ነው ውሃ ልኩ?
ሰባት ዓመት አልፈን እንኳ፣ ኑሮ ከኛ ነው እልኩ?
ሰው አልወለድ እያለ፣ ምጡ ብቻ እየፋፋ
የተወለደው ሳያድግ፣ ኑሮ ውድነቱ ከፋ!
አሴ!
የጃፓንን ጠባሳ ያየ፣ በውሃ አይጫወትም
ያገሬን መከራ ያየ፣ በድህነት አይቀልድም!
ያም ሆኖ አሴ ፈገግ በል፣ ካንተ ውለን መች ሊከፋን
ዛሬም አለ ሳቅ ውስጣችን!
መቼም ለምለም መጠውለጉ
ደረቁ አድሮ መሰንጠቁ
ግንዱ በቀኑ መውደቁ
ቅርንጫፉ መቀጠፉ
አይቀሬ ነው ምዕራፉ!
ይነጋል ብለን ስንጠብቅ
ምንም ሌላ ምሽት ቢፈልቅ
የቀረብነው ነገ ሲርቅ
አንተ ብትኖር እንዴት ትበሽቅ?!
አንተ ብትኖር እንዴት ትስቅ?!
አሴ! አይ ብታየው
የትላንቱ አዶከበሬ፣ የዛሬው ዛር እኩያ ነው፡፡
ተለውጠን ለመናወጥ፣
ተነዋውጠን ለመለወጥ
መግባባት ሆኖብናል ምጥ
ባለማወቅ ስንስማማ
በማወቅ የለንም ጀማ
አሴ
መቼም አድገን ብለናል፣ መወለዳችን ታብሎ
ይሄው ነው የዘመን ዜማ፣ የየአልባሳችን ደበሎ
ዕውነተኛ ዋሾ እንጂ፣ ዕውነት ለምቶ ያልታየበት
ክፉን ክፉ ማለት እንኳ፣ ክፉ ሆኖ ያፈርንበት!
አሴ ቀና በል እባክህ
የግፍ ዘመኔን ላዋይህ
ኖርን ያልነውን አለመኖር፣
በተኛህበት ላጫውትህ በተኛህበት
ላጫውትህ በተኛህበት ላንባልህ
ተስፋ መቼም መቀነት ነው
መሽከርክሪቱም ውል የለው
ይሁን እንስቃለን መቼስ፣ ያንተ ፈገግታ አይለየን
የነግ ነብሰ -ጡር ነን ዞሮ፣ የመኖር
ትጋት አይለቀን!
አሴ!
“እጅ በእጅ” እንል አልነበር፣ ከቶም
“ፍቅር እንዲደረጅ”
ዛሬ እጁንም አጣንና
መተማመኑም ጠፋና
አገር ጦም ማደር ጀመረ፣ ሻጭም ገዢም አጣንና
ዋ በኖርክ አሴ ምነው፣ ልባም ሁን ባልከው
አበሻን
ልብ እንዳጣ በነገርከው፣ ተስፋው እንኳን እንዳይመክን!
አገር አለኝ ለሚል ሁሉ
አበው እንደዚህ ይላሉ
“ወጣት ሆኖ አለማልቀስ
የጭካኔ ምሥክር ነው፤ ተፈጥሮን አለመዳሰስ ባንፃሩ ደግሞ የማይስቅ፣ በስተርጅና ማይደሰት
ጅላጅል ነው አለቀለት አገር አለኝ አይበል
በውነት
እኔ እማስበው አንተን ነው፣ እና ምኔም ከኛ ጋር ነህ
አሴ በሰባት አመትህ፣ እንካ ራስክን ላጋራህ
ሀሳባችን ነው ሀሳብህ!!
(ለአሠፋ ጐሣዬ ሰባተኛ ዓመት መታሰቢያ
እንካ ራስህን ላጋራህ!!)
አሴ በሰባት ዓመትህ - እንካ ራስክን ላጋራህ!
ዕውነት ለመናገር ግና፣ ሁለት ሰው ይበቃል ይሏል
አንድ አድማጭ፣ አንድ ነጋሪ፤ ጉዳዩን ይጨርሱታል፡፡
ዕውነተኛ ግጥም አሴ፣ ሙቅ ብርድ ልብስህ ነውና
ዋና ፍስሀ ይሆናል፣ ለውስጣችን ግለት ጤና!
አሴ! ይገርምሀል ደግ አጠረ
የቁም ሙት እየወፈረ
ቁመት ወርድ እየጨመረ
ለቀስተኛ እየጨፈረ
የዕውነት ሟች ከርሞ እየከሳ
ስሙም መልኩም ጥቅሙም ሳሳ!
እያደር ይሞላል ያልነው፤ ያፈሳል እንዴ ታሪኩ
ሽንቁር አለው ወይ ትውልዱ፣ ዕውነት የት ነው ውሃ ልኩ?
ሰባት ዓመት አልፈን እንኳ፣ ኑሮ ከኛ ነው እልኩ?
ሰው አልወለድ እያለ፣ ምጡ ብቻ እየፋፋ
የተወለደው ሳያድግ፣ ኑሮ ውድነቱ ከፋ!
አሴ!
የጃፓንን ጠባሳ ያየ፣ በውሃ አይጫወትም
ያገሬን መከራ ያየ፣ በድህነት አይቀልድም!
ያም ሆኖ አሴ ፈገግ በል፣ ካንተ ውለን መች ሊከፋን
ዛሬም አለ ሳቅ ውስጣችን!
መቼም ለምለም መጠውለጉ
ደረቁ አድሮ መሰንጠቁ
ግንዱ በቀኑ መውደቁ
ቅርንጫፉ መቀጠፉ
አይቀሬ ነው ምዕራፉ!
ይነጋል ብለን ስንጠብቅ
ምንም ሌላ ምሽት ቢፈልቅ
የቀረብነው ነገ ሲርቅ
አንተ ብትኖር እንዴት ትበሽቅ?!
አንተ ብትኖር እንዴት ትስቅ?!
አሴ! አይ ብታየው
የትላንቱ አዶከበሬ፣ የዛሬው ዛር እኩያ ነው፡፡
ተለውጠን ለመናወጥ፣
ተነዋውጠን ለመለወጥ
መግባባት ሆኖብናል ምጥ
ባለማወቅ ስንስማማ
በማወቅ የለንም ጀማ
አሴ
መቼም አድገን ብለናል፣ መወለዳችን ታብሎ
ይሄው ነው የዘመን ዜማ፣ የየአልባሳችን ደበሎ
ዕውነተኛ ዋሾ እንጂ፣ ዕውነት ለምቶ ያልታየበት
ክፉን ክፉ ማለት እንኳ፣ ክፉ ሆኖ ያፈርንበት!
አሴ ቀና በል እባክህ
የግፍ ዘመኔን ላዋይህ
ኖርን ያልነውን አለመኖር፣
በተኛህበት ላጫውትህ በተኛህበት
ላጫውትህ በተኛህበት ላንባልህ
ተስፋ መቼም መቀነት ነው
መሽከርክሪቱም ውል የለው
ይሁን እንስቃለን መቼስ፣ ያንተ ፈገግታ አይለየን
የነግ ነብሰ -ጡር ነን ዞሮ፣ የመኖር
ትጋት አይለቀን!
አሴ!
“እጅ በእጅ” እንል አልነበር፣ ከቶም
“ፍቅር እንዲደረጅ”
ዛሬ እጁንም አጣንና
መተማመኑም ጠፋና
አገር ጦም ማደር ጀመረ፣ ሻጭም ገዢም አጣንና
ዋ በኖርክ አሴ ምነው፣ ልባም ሁን ባልከው
አበሻን
ልብ እንዳጣ በነገርከው፣ ተስፋው እንኳን እንዳይመክን!
አገር አለኝ ለሚል ሁሉ
አበው እንደዚህ ይላሉ
“ወጣት ሆኖ አለማልቀስ
የጭካኔ ምሥክር ነው፤ ተፈጥሮን አለመዳሰስ ባንፃሩ ደግሞ የማይስቅ፣ በስተርጅና ማይደሰት
ጅላጅል ነው አለቀለት አገር አለኝ አይበል
በውነት
እኔ እማስበው አንተን ነው፣ እና ምኔም ከኛ ጋር ነህ
አሴ በሰባት አመትህ፣ እንካ ራስክን ላጋራህ
ሀሳባችን ነው ሀሳብህ!!
(ለአሠፋ ጐሣዬ ሰባተኛ ዓመት መታሰቢያ
እንካ ራስህን ላጋራህ!!)
ነ.መ
Read 9720 times Last modified on Tuesday, 20 December 2011 06:23