Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Saturday, 17 December 2011 10:47

ብርሃን እና ሰላም ለደራስያን ማህበር የ300 ሺ ብር ተዘዋዋሪ ሂሳብ ፈቀደ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ለኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ለመፃህፍት ህትመት የሚውል ተዘዋዋሪ ሂሳብ ፈቀደ፡፡ ድርጅቱ ለማህበሩ የፈቀደው 300ሺ ብር ተዘዋዋሪ ሂሳብ አዳዲስ የመፃሕፍት ሥራዎችን ለሕትመት ብርሃን የሚያበቃ ሲሆን ማህበሩ በራሳቸው ገንዘብ ማሳተም ያልቻሉ አባላቱን ሥራዎች በማወዳደር እንደሚያሳትምበት ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ከዚህ ቀደም ከአርቲስቲክ ማተሚያ ድርጅት ባገኘው የ205ሺህ ብር ተዘዋዋሪ ሂሳብ ስምንት መፃሕፍትን ያሳተመ ሲሆን አብዛኞቹ እስካሁን 60በመቶ የሕትመት ዋጋ መመለሳቸውን የማህበሩ ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረክርስቶስ ሃይለስላሴ ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡  ከነዚህ መፃሕፍት “ሽንኩርት” “የገቦ ፍሬ”፣ “ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ” “መሃን እናት”፣ “የሕይወት ገፆች”፣ “ተጠባባቂ አይኖች”  እና “ፍቅር እና መዳፍ” ናቸው፡፡ ከነዚሁ መካከል የደራሲና ጋዜጠኛ ኢሳይያስ ሆርዶፋ “ዮሚላታ” የኦሮምኛ ልቦለድ ወዲያውኑ ሙሉ ለሙሉ ተሸጦ እንዳለቀ ማወቅ ተችሏል፡፡ አዲሱን ተዘዋዋሪ የሕትመት ሂሳብ አስመልክቶ ከትናንት ወዲያ ረፋድ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በተከናወነ ሥነ ሥርአት ማህበሩ እነዚህን መፃሕፍትና ሌሎች ሕትመቶቹ ለማተሚያ ድርጅቱ ቤተመፃሕፍት አበርክቷል፡፡  ብርሃንና ሰላም የተመሠረተበትን 90ኛ ዓመት በቅርቡ ለማክበር በዝግጅት ላይ ነው፡፡

 

 

Read 3379 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 10:49