Saturday, 07 June 2014 13:35

የአውራምባ ማህበረሰብ 42ኛ የምስረታ በአል ይከበራል

Written by  አለማየሁ አንበሴ
Rate this item
(0 votes)

የአውራምባ ማህበረሰብ የተመሰረተበት 42ኛ ዓመት ከሰኔ  1 ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ገነት ሆቴል በድምቀት ይከበራል፡፡
ለሶስት ቀናት “ቱሪዝም ለተሻለች ኢትዮጵያና ለአለም አቀፍ መግባባት” የሚለውን መሪ ቃል በማንገብ የሚከበረው በአል ሰኔ 1 ቀን በማርሽ ባንድ በመታጀብ የመክፈቻ ስነ-ስርአቱ የሚከናወን ሲሆን ሰኔ 2 ደግሞ በአውራምባ ማህበረሰብ ላይ የሚቀርቡ ጥናታዊ ፅሁፎችና ውይይቶች ይካሄዳሉ ተብሏል፡፡ በቀጣይ ቀንም በቱሪዝምና በማህበረሰቡ ተጠቃሚነት ላይ የፓናል ውይይት የሚካሄድ ሲሆን በሶስቱም ቀናት ኤግዚብሽንና ልዩ ልዩ በአሉን የተመለከቱ ዝግጅቶች ይቀርባሉ፡፡
በበአሉ ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ መሆኑን ያስታወቀው የበአሉ አዘጋጅ ኮሚቴ፤ የዘጠኙ ብሔራዊ ክልሎች ተወካዮች፣ የቱር ኦፕሬሽን ተቋማት፣ ሆቴሎች፣ የትምህርት ተቋማትና ከኢንዱስትሪው ጋር ተያያዥ ስራ የሚያከናውኑ ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ይገኛሉ ተብሏል፡፡

Read 2715 times