Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 17 December 2011 10:44

የኢትዮጵያ የሙዚቃ ቡድኖች በስፔን ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ከአንድ ወር በኋላ በሚደረግ የሙዚቃ ቡድኖች ውድድር አሸናፊ የሚሆኑ 14 ኢትዮጵያዊ የሙዚቃ ቡድኖች በስፔን ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡ አሸናፊዎቹ ቡድኖች በስፔን የሚያቀርቡትን የሙዚቃ ድግሶች ወጪ የስፔን ፕሮዲዩሰሮች እንደሚሸፍኑ ታውቋል፡፡ የተወዳዳሪዎች የድረገፅ ምዝገባ ትናንት የተጀመረ ሲሆን ተወዳዳሪ የሙዚቃ ቡድኖች የባህል ወይም የዘመናዊ ሙዚቃ ሥራዎቻቸውን ቪዲዮ ክሊፕ፣ ፎቶግራፎች፣ ሥዕሎች ወዘተ በድገረፅ ወይም በሲዲ ከጥር 13 ቀን 2004 ዓ.ም በፊት መላክ ይችላሉ ተብሏል፡፡ ከትናንት ወዲያ ሽሮ ሜዳ በሚገኘው የስፔን ኤምባሲ በተሰጠው መግለጫ ላይ  የተገኙት በኢትዮጵያ አዲሱ የስፔን አምባሳደር ሚጉየል ፌርናንዴዝ ፓላሲዮስ፤ ይኼ ተነሳሽነት የኢትዮጵያን ሙዚቃ ለስፔን ሕዝብ ለማድረስ ትልቅ እድል ይከፍታል ብለዋል፡፡ የሙዚቃ ውድድሩን ካዛ አፍሪካ የተሰኘ የስፔን ድርጅት ከሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያው አካሽያ ጃዝና የዓለም ሙዚቃ ፌስቲቫል ጋር ያቀርቡታል፡፡

 

 

Read 1796 times Last modified on Saturday, 17 December 2011 10:46

Latest from